Saturday, 30 July 2016 11:40

ቆሻሻ መጣል ክልክል ነው!

Written by  ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
Rate this item
(13 votes)

    የሰዎችን አስተሳሰብ ሊለውጡ የሚችሉ ንግግሮችን በማድረግ የሚታወቀው ዓምደኛው ዴቪድ ጄ. ፖላይ ‹የቆሻሻ መኪና ሕግ (The Law of the Garbage Truck)  የተሰኘ ተወዳጅና ተደናቂ መጽሐፍ አለው፡፡ ይህንን መጽሐፉን ለመጻፍ መነሻ የሆነው ኒውዮርክ ውስጥ አንድ ቀን በታክሲ ሲጓዝ ያጋጠመው አደጋ ነበር፡፡ እርሱ የሚሄድበትን ታክሲ ከጎኑ የመጣ ሌላ መኪና ሊገጨው ለጥቂት ተረፈ፡፡ ስሕተቱ ከጎን የነበረው መኪና ሾፌር ነበር፡፡ ነገር ግን አደጋ አድራሹ ሾፌር በስሕተቱ ከመፀፀት ይልቅ መስኮቱን ከፍቶ የታክሲውን ሾፌር መሳደብና ማበሻቀጥ ጀመረ፡፡ የታክሲው ሾፌር ግን ፈገግ ብሎ እጁን ለሰላምታ በማውለብለብና ‹መልካም ቀን ይሁንልህ› በሚል የምኞት ቃል አለፈው፡፡
ጄ. ፖላይ ነገሩ ስላስገረመው የታክሲው ሾፌር ጠየቀው፡፡ ‹ጥፋተኛው ያኛው ሾፌር ነው፡፡ ይባስ ብሎም መስኮቱን ከፍቶ ሲሰድብህ ነበር፡፡ አንተ ግን መልካም እንደተደረገልህ ሁሉ ፈገግ አልክለት፤ እንዲያውም እጅህን አውጥተህ ሰላምታ ሰጠኸው፡፡ መልካም ምኞትህንም ገለጥክለት፡፡ ግን ለምን?› ሲል ጠየቀው፡፡ የታክሲውም ሾፌር አሁንም ፈገግ ብሎ ‹ብዙ ሰዎች የቆሻሻ መኪኖች ናቸው፡፡ ቆሻሻውን ተሸክመውም የሚያራግፉበት ቦታ ይፈልጋሉ፡፡ የያዙት ቆሻሻ ስድብ፣ ንዴት፣ ጭንቀት፣ ብልግና፣ ጭቅጭቅ፣ ንዝንዝ፣ ቁጣ፣ ርግማን፣ ተንኮልና ነገር ሊሆን ይችላል፡፡ ልክ የቆሻሻ መኪና ከየቤቱ ቆሻሻውን እስኪሞላ ድረስ እንደሚሰበስበው ሁሉ እነዚህም ከቤታቸው፣ ከትዳር አጋራቸው፣ ከጓደኞቻቸው፣ ከሥራ ቦታቸው፣ ከንግድ ድርጅታቸው፣ ከብሶታቸው፣ ከኪሣራቸው፣ ከደረሰባቸው ችግርና ካጋጠማቸው ፈተና ቆሻሻቸውን ይሰበስቡታል፡፡
አንተ ግን የቆሻሻ መጣያቸው አትሁን፡፡ የቆሻሻ መኪናው ሲሞላ የመጣያ ቦታ ይፈልጋል፡፡ ከዚያ ደግሞ ተመልሶ እንደገና ሌላ ቆሻሻ ይሰበስባል፡፡ እነዚህም ከየቦታው ቆሻሻ ጠባያቸውን ይሰበስቡና አንተ ላይ ሊያራግፉብህ ይመጣሉ፡፡ ያን ጊዜ ዝም ብለህ አትቀበላቸው፡፡ የቆሻሻ መኪና ከየቦታው የሰበሰበውን ቆሻሻ ሲያነሣ፣ ቆሻሻ የነበረበትን ቦታ ያቃልለዋል፡፡ ነገር ግን ወስዶ ሌላ ቦታ በማከማቸት የተከማቸበትን ቦታ ያቆሽሸዋል፣ ያሸተዋል፣ ያበላሸዋል፡፡ እነዚህም እንዲሁ ናቸው፡፡ ከየቦታው የሰበሰቡትን ቆሻሻ ጠባይ አንተ ላይ ያራግፉና አንተን ሲያናድዱህ፣ ሲያበሽቁህ፣ ሲያስፀፅቱህ ይውላሉ፡፡ ቀንህን ያበላሹብሃል፡፡ ያደረጉህ ነገር፣ የሠሩህ ሥራና፣ የወረወሩብህ ስድብ አአምሮህ ውስጥ እየተብላላ ቀኑን ሙሉ ጠባይህን አበላሽቶት ይውላል፡፡
ለምን ትፈቅድላቸዋለህ? ፈገግ ብለህ፣ ምንም እንዳልተፈጠረ ቆጥረህ፣ ነገሩን አሳልፈህ፣ ለክፋታቸው በጎነት፣ ለስድባቸው መልካም ምኞት፣ ለርግማናቸው ምርቃት፣ ለቁጣቸው ፈገግታ፣ ለትዕቢታቸው ትኅትና መልስላቸውና ቆሻሻቸውን ይዘው እንዲመለሱ አድርጋቸው፡፡ በጭራሽ አንተ ላይ ማራገፍ የለባቸውም፡፡ ለዚህ ነው እኔም በፈገግታ፣ በሰላምታና በመልካም ምኞት የሸኘሁት፡፡ ከቻልኩ በርሱ ላይ ያለውን ቆሻሻ አቀልለታለሁ፡፡ ስላልሰደብኩት፣ ስላላንጓጠጥኩትና ስላልተጨቃጨቅኩት ቀኑን ሙሉ ፈገግታዬን፣ ሰላምታዬንና መልካም ምኞቴን በማሰብ ሲደሰት ይውላል፡፡ ካልተቻለ ደግሞ እኔ ላይ ቆሻሻውን ከማራገፍ ስለተከላከልኩት አትራፊው እኔ ነኝ› ሲል አብራራለት፡፡
ይህንን የሰማው ጄ. ፖላይ ነገሩን ሲያምሰለስለው ከርሞ፤ ‹የቆሻሻ መኪና ሕግ› የተሰኘውን ተወዳጅ መጽሐፉን አዘጋጀ፡፡ ፖላይ በዚህ መጽሐፉ ውስጥ ‹የቆሻሻ መኪና በአንተ ላይ ቆሻሻውን እንዳያራግፍ ከፈለግክ እነዚህን ሕጎች ተግብራቸው› ይላል፡፡ የመጀመሪያው ሕግ ባለጌ፣ ሐሳብ አልባና ቁጡ የሆኑ ሰዎች በአንተ ላይ ቆሻሻቸውን እንዳይጥሉ ምንጊዜም ተከላከል› የሚል ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት ሰዎች ሲያግጥሙህ ከቻልክ ጆሮህን ካልቻልክም ልብህን አትስጣቸው፡፡ ‹ወፎች በጭንቅላታችን ላይ እንዳይበሩ ማድረግ አንችልም፡፡ በጭንቅላታችን ላይ ጎጆ እንዳይሠሩ ማድረግ ግን እንችላለን› የሚል አባባል አለ፡፡ ሰዎች እንዳይሳደቡ፣ እንዳይቆጡ፣ ነገር እንዳያመነጩና እንዳይነታረኩ ማድረግ አንችልም፡፡ ጭንቅላታቸው እነርሱ ላይ ስለሆነ፡፡ ነገር ግን ከእነርሱ አንደበት የሚወጣው ክፉ ቃል በጆሯችን በኩል ወደ ልባችን ገብቶ፣ ጎጆ እንዳይሠራ ማድረግ  ይቻላል፡፡ ስናስበው፣ ስናወጣ ስናወርደው፣ ከንፈራችንን ስንነክስለት፣ ጠረጲዛ በቡጢ ስንመታና ምነው እንዲህ ባልኩት ኖሮ፣ እንዲህም ባደረግኩት ኖሮ ስንል እንዳንውል ማድረግ ይቻላል፡፡ እንዴት? ፊት ባለመስጠት፣ ጆሮና ዓይን በመንሣት፣ የልብን በር በመዝጋት፣ ከቁብ ባለመቁጠር፣ ለመርሳት በመሞከር፣ በጭንቅላታችን ላይ እንደሚበሩት ወፎች በመቁጠር፡፡ በመናቅና በማቃለል፡፡
ሁለተኛው ሕግ ደግሞ፤ ‹ያለፉ ክፉ ነገሮችን ማስታወስና ቀጣዩን የሕይወት ጉዞህን መፍራት አቁም› ይላል፡፡ ያለፉ ክፉ ትውስታዎችን በአንዳች ነገር ዝጋቸው፡፡ በንስሐ፣ በይቅርታ፣ በካሣ፣ በዕርቅ፡፡ እርሳቸው፡፡ ካልቻልክ ደግሞ በሚጎዱህ መጠን ልክ አታስታውሳቸው፡፡ መርሳት የሚባለው ጸጋ የተሰጠን አንድም ክፉ ነገሮችን ለመርሳት እንድንችል ነው፡፡ ቆሻሻውን አጽዳ፡፡ ሰዎች በአንድ ወቅት ክፉ አድርገውብህ ይሆናል፡፡ እነዚያ ሰዎች በአንተ ላይ ቆሻሻውን አከማቹት ማለት ነው፡፡ አንተም ለዘመናት የቆሻሻቸው ማራገፊያ ሆነህ፣ ይዘኸው እየተጓዝክ ነው፡፡ አራግፈው፡፡ ቆሻሻ ምንም ቢራገፍ በቆሻሻ መኪናው ላይ የሚተርፍ ቅሬት መኖሩ አይጠረጠርም፡፡ አንተም ባለፉት ዘመናት ሰዎች ላይ ቆሻሻ ስታራግፍ አንተ ላይ የቀሩ ትርፍራፊዎች አይጠፉም፡፡ ተሸክመኻቸው አትዙር፤ አራግፋቸው፡፡ ያለፉ ቆሻሻዎችን አለማጽዳት ነገን እንድንፈራው ያደርገናል፡፡ ያለፉ ቆሻሻዎችን በሚገባ ካጸዳናቸው ነጻነት፣ ንጽሕናና ብሩኀ ተስፋን እናገኛለን፡፡ ብዙ ሰዎች የትናንት እሥረኞች ናቸው፡፡ እርሾው መልካም ካልሆነ ሊጡ፣ ብሎም እንጀራው እንደሚበላሸው ሁሉ ትናንትህ ካልጸዳ ነገህ ይበላሻል፡፡
ሦስተኛው ሕግ ደግሞ ›ልትቆጣጠረው በምትችለው ነገር ላይ አተኩር እንጂ ልትቆጣጠራቸው በማትችል ክፉ ነገሮች ላይ ጊዜ አታጥፋ› የሚል ነው፡፡ ሰዎች በሚናገሩት፣ በሚያደርጉት፣ በሚሠነዝሩትና በሚፈጥሩት ነገር ላይ ልብህ አይቁም፡፡  በታክሲ ውስጥ ስትሄድ አንድ ጋጠ ወጥ ሰው ቢገጥምህና የማይሆን ቃል ቢናገርህ ለእርሱ ቦታ አትስጠው፡፡ አንዱ ፌርማታ ላይ ይወርዳል፡፡ ከዚያ በኋላ አታገኘውም፡፡ አንተን ግን ቀኑን ሙሉ ሲበጠብጥህ ይውላል፡፡ ‹ቁንጫ የጠረጉት ለት ባለጌ የመከሩት ለት ይብሰዋል› እንዲሉ ምክር ለሁሉ አይሰጥም፣ መልስ ለሁሉ አይመለስም፤ ክርክር ከሁሉም ጋር አይደረግም፡፡ ዕንቁዎችህን የምትሰጣቸውን ሰዎች ለይ፡፡ ዕንቁላሎችህን የምታስታቅፋቸውን ዶሮዎች ምረጥ፡፡ የዚያን ሰው ተግባር፣ ንግግር፣ ጠባይ፣ ባህልና ልምድ ልትቆጣጠረው አትችልም፡፡ ልጅህ ነው? ጓደኛህ ነው? የትዳር አጋርሽ ነው? የሥራ ባልደረባህ ነው? ጎረቤትህ ነው? በጉዳዩ ላይ ብትበረታበት ለውጥ ለማምጣት ትችላለህ? ከሆነ መልካም፡፡ ካልቻልክ ግን ለምን ዕንቁዎችህን በእሪያዎች ፊት ትጥላለህ? ‹እገሌ እንዲህ ይልሃል›፣ ‹እዚህ ቦታ ስላንተ እንዲህ ሲወራ ሰማሁ› የሚሉትን አትስማ፡፡ አትቆጣጠራቸውም፡፡ ራስህን ተቆጣጠር፣ ራስህን ግራና የራስህን መንገድ ቀይስ፡፡
አራተኛው ሕግ ‹ባገኘህበት ቦታ ሁሉ ጋጠ ወጥነትን ቀንስ፣ ሥልጣኔን ጨምር፣ ጉልቤዎችን ከነ ቆሻሻ መኪናቸው አስቁማቸው› ይላል፡፡ ሰዎች በአንተ ላይ ጋጠወጦችና ያልሠለጠኑ እንዲሆኑ አትፍቀድላቸው፡፡ መርሕህን፣ ጠባይህንና መሥመርህን ግልጽ አድርግላቸው፡፡ ጋጠወጥነትንና አለመሠልጠንን በቸልታና በዝምታ ከተቀበልካቸው እንደ ልባቸው ይፈነጩብሃል፡፡ ከመጀመሪያው እንዲህ ላሉ ሰዎች ቦታ አይኑርህ፤ ካጋጠሙህም ሐሳብህን ግለጥላቸው፡፡ ካልተመቸሃቸው ወይም ካልተመቹህ ግንኙነትህን አቋርጥ፡፡ ‹ለባለጌ ከሳቁለት፣ ለውሻ ከሮጡለት› አደጋው ከባድ ነው፡፡ ሥልጣን ወይም ጉልበት ስላላቸው ብቻ በአንተ ላይ ቆሻሻ ለመድፋት እንደሚችሉ የሚያስቡ ባለ ሥልጣናት፣ አለቆች፣ ጉልበተኞችና ደፋሮች ይኖራሉ፡፡ ከቻልክ በሕግ ካልቻልክ ግን በርህን በመዝጋት መኪናውን አስቁመው፡፡ የሚፈልጉትን አታድርግላቸው፣ በመንገዳቸው አትሂድ፣ በዕቅዳቸው አትመራ፣ ጠባያቸውን አትጋራ፣ እንዳመጣጣቸው አትመልስ፡፡ ምንጊዜም አንተ ራስህን ብቻ ሁን፡፡ የወረወሩትን አታስበው፣ የጠየቁህንም ሁሉ አትመልስ፡፡ ችግሩን የመፍቻ ሌላ መንገድ አስብ፡፡ የሠለጠነ፣ ሕጋዊ የሆነና፣ ችግሩን የሚፈታ መንገድ ፈልግ፡፡ ጋጠወጥነትን በጋጠወጥነት፣ ስድብን በስድብ፣ ነገርን በነገር፣ ክፋትንም በክፋት አትመልስ፡፡ ያ ከሆነ በመንገዳቸው እየተጓዝክ፣ የቆሻሻቸውም ማራገፊያ እየሆንክ ነው፡፡ ሁለታችሁም ጋ አንድ ዓይነት ሽታ ካለ፣ ሁለታችሁም ጋ አንድ ዓይነት ቆሻሻ አለ ማለት ነው፡፡
አምስተኛው ሕግ ደግሞ ‹በቤተሰቦችህ፣ በልጆችህ፣ በጓደኞችህና በሥራ ባልደረቦችህ ላይ ቆሻሻ ባለመድፋት ጠባይህን እየገራኸው ሂድ› ይላል፡፡ ከቻልክ ከአንተ ቆሻሻ እንዳይወጣ አድርግ፡፡ ካልቻልክስ? ቆሻሻው ማንንም ሳይጎዳ የሚወገድበትን መንገድ ፈልግ፡፡ በተናደደክ ጊዜ ከሰዎች ጋር መከራከርን ተው፡፡ ተደስተህም ሆነ ተናደህ ውሳኔ አትወስን፡፡ ከስሜትህ ሳትበርድ ሰዎችን አታናግር፡፡ ከሰዎች ጋር ለመነጋገሪያ መልካሙ ጊዜ ስሜት በርዶ፣ አእምሮ ቦታውን ሲይዝ ነው፡፡ የተናደድክበትን ሰው ወዲያው አታግኘው፡፡ ውለህ አድረህ፣ ነገሩን አውጥተህና አውርደህ፣ ከተለያየ አቅጣጫም ነገሩን መዝነህ ከዚያ በኋላ አናግረው፡፡ ስድብ ሰውን አይለውጥም፤ ቁጣም አእምሮን አይቀይርም፤ ጭቅጭቅ እንደሚያንጠባጥብ የቤት ጣሪያ ይሆናል፤ ሐሜትም ዞሮ ለራስ ነው፡፡ ለውጥ ማምጣት፣ ችግር መፍታትና ሰዎችን ማረም ከፈለግክ ሌሎች መንገዶችን ሞክር፡፡
‹ከመርገም ውስጥ በረከትን ፈልግ› ይላል ስድስተኛው ሕግ፡፡ ከኪሣራህ፣ ከሕመምህ፣ ከጉዳትህና ከችግርህ ውስጥ ደስታን ለማብቀል ሞክር፡፡ አካልህን ሲያሥሩህ፣ ኅሊናህን ነጻ አድርግ፤ ሰውነትህን ሲያምህ፣ አእምሮህን ጤነኛ አድርገው፤ ገንዘብህን ስትከስር ጤናህንና ሥነ ልቡናህን  አትርፍ፤ ወዳጆችህን ስታጣ፣ ትዝታቸውን አስቀር፤ አካልህ ሲጎዳ መንፈስህን ሙሉ አድርግ፤ ያጣህውን ትተህ ያለህን ቁጠር፡፡ ማንም ጥርስህን እንጂ ፈገግታህን ማርገፍ አይችልም፡፡ ማንም ዋንጫህን እንጂ አሸናፊነትህን ሊወስድብህ አይችልም፡፡
‹የቆሻሻ መኪና የማይደርስበት ክልል መሥርት› የሚለው ደግሞ ሰባተኛው ሕግ ነው፡፡ በቤተሰብህ፣ በጓደኞችህ፣ በዘመዶችህ፣ በሥራ አካባቢህና በመንደርህ ይህንን ክልል መሥርት፡፡ ሌሎችን በማሳመን፣ በማስረዳት፣ ሐሳብህን በመግለጥና ነገሩ እንዲገባቸው በማድረግ ‹የቆሻሻ መኪና በዚህ ማለፍ ክልክል ነው› የሚል መርሕ እንዲኖራቸው ማድረግ ትችላለህ፡፡ የምትውልበት፣ የምትሠራበትና የምትኖርበት አካባቢ ከቆሻሻ መኪኖች ነጻ ከሆነ ማንም ወደ አንተ ቆሻሻ ለመድፋት አይመጣም፡፡ በቢሮህ ግድግዳ ላይ ‹ቆሻሻ መድፋት ክልክል ነው› የሚል ለጥፍ፡፡ ሰዎች ይገርማቸውና ይጠይቁሃል፡፡ ‹እዚህ ቢሮ የቆሻሻ መኪና ምን ሊያድርግ ይመጣል? የጽዳት ሠራተኞችስ እንዴት እዚህ ቦታ ቆሻሻ ይደፋሉ? › ይሉሃል፡፡ ንገራቸው፡፡ ቆሻሻው ምን እንደሆነና የቆሻሻ መኪኖች እነማን እንደሆኑ፡፡ ይቀየሩ ይሆናል፡፡ ከጓደኞችህም ጋር ተነጋገሩና ተስማሙበት፡፡ ማንም ቆሻሻውን በራሱም ላይ ሆነ በሌሎች ላይ ላይጭን ተስማሙ፡፡
የመጨረሻው ሕግ ደግሞ ‹በየቀኑ ለመደስት ሞክር፣ የምትወደውን ለመሥራትና የምትሠራውን ለመውደድ ተጣጣር፣ ተግባርህም ሁሉ ለውጥ የሚያመጣ ይሁን› ይላል፡፡ በየቀኑ መደሰት ማለት በየቀኑ መጠጣት፣ አዲስ ልብስ መልበስ፣ ሲኒማ መመልከትና ቀልድ ሲቀልዱ መዋል አይደለም፡፡ አዲስ ነገር ለመሥራትና ትርጉም ያለው ውሎ ለመዋል ወስኖ መነሣት ነው፡፡ መሥሪያ ቤትህ ዕቅድ ይኖረው ይሆናል፡፡ አንተስ አለህ? ወደ ቢሮ የምትሄደው ያስቀመጥከውን ለመሥራት ነው ወይስ የተቀመጠልህን ለመሥራት? ስንት ፋይል ልታይ፣ ስንት ውሳኔ ልትወስን፣ ስንት ምርት ልታመርት፣ ስንት ችግር ልትፈታ፣ ስንት ትርፍ ልታመጣ፣ ስንት ሰው ልታክም፣ ለራስህ ምን አቅደሃል? አካባቢህን ጽዱ፣ ውብ፣ ሥራብኝ ሥራብኝ የሚል አድርገኸዋል? ሥራ ቦታህ ላይ ከቀኑ ውስጥ ሩቡን ትውልበታልህ፤ ያ ማለት ከሕይወትህ ሩቡን ታሳልፍበታለህ፤ የሥራ ቦታህን ስታበላሸው ሩቡን ኑሮህን ታበላሸዋለህ፡፡ ያም ብቻ አይደለም፡፡ ሥራህን በወደድከው መጠን ጠዋት ወደ ሥራህ እንደ ጽጌሬዳ ይስብሃል፡፡ ማታም ወደ ቤትህም በደስታ ይሸኝሃል፡፡
ከቻልክ የምትወደውን ሥራ ሥራ፡፡ ካልቻልክ የምትሠራውን ሥራ ውደድ፡፡ ለመጥላት ምክንያት ከምትፈልግ ለመውደድ ምክንያት ፈልግ፡፡ የምትጠላውን ሥራ እየሠራህ ምንም በጎ ለውጥ ልታመጣ አትችልምና፡፡ ደንበኞችህ ቆሻሻ ተጭነው ይመጡ ይሆናል፡፡ አንተ ግን እንዲያራግፉብህ አትፍቀድላቸው፡፡ ንዴታቸውን አብርደህ፣ ቁጣቸውን አሳስቀህ፣ ችግራቸውን ፈትተህ፤ ያንንም ሁሉ ካልቻልክ ኀዘናቸውን ተካፍለህ መልሳቸው፡፡ ቢሮህን የቆሻሻ ማከማቻ አታድርገው፡፡ ስብሰባ የደስታ ምንጭ፣ የዕውቀት መገብያና፣ የችግር መካፈያ እንጂ የቆሻሻ መጣያ እንዳይሆን ሥራ፡፡ ደስታ ከለውጥ ይገኛል፡፡ የምትጋተረው ከችግሮች ጋር እንጂ ከሰዎች ጋር አይሁን፡፡ ለውጥ እያመጣህ በሄድክ ቁጥር ለራስህ ደስታን እየሸመትክ ትሄዳለህ፡፡
ይህንን ለማድረግ የቆረጡ ሰዎች ይህንን መፈክር ይዘዋል፡፡
ቁም! እዚህ ቦታ ቆሻሻ መጣል ክልክል ነው፡፡

አዎ! በሚያሳዝን ሁኔታ!
የአባተን እንደዚህ ከጨረስኩልህ ተስፋዬ ይፍሩስ እንዴት ሆነ ነው? የቤተሰቦቹን ዕጦት፣ የቤተሰቦቹን ኪሳራ እናስላው … አንድ አናፂ አባት፤ ሁለት ልጆቹን በድህነት አስተምሮ ተስፋዬ ይፍሩ መሀንዲስ እዚህ ጎፋ ተመደበ፤ አመፅ ተነሳ፡፡ የአመፁ አስተባባሪ እሱ ነው፡፡
“ተስፋዬ?”
አዎ ታላቅየው፣ አባተን ያስተማረው ማለት ነው። ሲያምፁ እሱ ለጥበቃ የተመደበበት ቦታ አሁን ልክ በድሉ ህንፃ የተባለው ቦታ ነው፡፡ እነ መንግስቱ ኃ/ማ፣ ደርጎች ደረሱ፤ አመፁ ላይ፡፡ አመፁን ሊያከሽፉና ተስፋዬ ይፍሩን የአመፁን አስተባባሪ፣ እጅ ከፍንጅ ሊይዙት ሲሉ ራሱን ገደለ!!
ያ ትውልድ እሺ፤ እንዴት ነው በካህሳይ ድላይ የሚመዘነው? እዚች አገር የማዝነው እነ ገረመው የሚባሉ 14000 ብር (የፊውዳል ልጅ ነው፣ የባላባት ልጅ ነው) አባትዬው ሁሉን ነገር ሲወረሱ፣ ያንን ገንዘብ ከሳጥን ውስጥ ወስዶ፤ ለኢህአፓ ለከተማው አስረክቦ አሲምባ የመጣው ልጅ ጭንቅላቱን ሲመታ፣ በአንድ እጁ በሁለት እግሩ ማህል ገብቼ ላድነው ስል የሁለታችንም ግንባር እኩል በሆነበት ላይ አንዷ ጥይት የእሱን ግንባር መትታው፣ የሱ ግማሽ ግንባር እግሩ ላይ ሲወድቅ፤ እኔ ወይ ሰቦቃ፣ ወይ ለማ ወይ ደርቤ የፈለከውን በለኝ፤ ከዛ በላይ እኔ ተርፌ፣ ያ ደም እኔ ላይ ፈሶ፣ በደምቡ መሰረት ስኖር፤ ትልቅ ነገር ነው - ያ ደም እሜዳ ፈስሶ እንዴት ይሆናል? ላለየው ሰው ለማስረዳት ይከብዳል፡፡ ካልኖርከው በስተቀር አባተ ይፍሩን ለማን ትነግራለህ? ተስፋዬ ይፍሩን ለማን ትነግራለህ? ድላይና ካህሳይ (አማኑኤል በሚል ስም ነው የማውቀው እኔ) ሁለቱ የጭንቅላታቸው አቅም ከመዋደድ ያላለፈ ነው እሺ! አገር ህዝብ፤ Ideologyን አልደረሱበትም - ገና መዋደድ ላይ ናቸው፡፡ ስለዚህ ተዋደውም ከሆነ፣ መፋቀሩም ተሰርቶ ከሆነ፤ ባይዋደዱ አይገርመኝም፡፡ ግን እዛ ጋ በአንተ ግጥም ያልተዘመረለት ብለህ ፅፈሃል- እኔ መኃይም በመሆኔ፣ምሁር ባለመሆኔ ያልጻፍኩትን፣ ስለ እነ አባተ ይፍሩ ብታውቅ ያልተዘመረለትን ምን ልትል ነው? የተዘመረላቸውስ እነ ጃራ አሉ! አሪፍ ልጆች ናቸው!
“ያ፤ ተራራ የተሰየመለት ጀግና ነው ያልከኝ? ነው እንዴ?”
ደረጄ ሞሲሳ ነው ዕውነተኛ ስሙ፡፡ የላብ ስኩል (የበዕደማሪያም) ልጅ ነው፡፡ የበረሀ ስሙ ጃራ ነው! ሮባ ልጁን በስሙ ጃራ ብሎ ነው የሰየመው - ዛሬ!
“የሮባ ልጅ?”
የሮባ ልጅ ጥፋት ቢያጠፋኮ ይሄን ስም አነሳብሃለሁ ነው ያለው፡፡ ይበዛብሃል! ይሄ የተዘመረለት ጃራ ነው፡፡ ያልተዘመረላቸው አባተና

Read 15702 times