በቾምቤ ፕሮዳክሽን የቀረበው “ያመለጠው እስረኛ” የተሰኘው ልብ ሰቃይ ቴአትር ባለፈው ማክሰኞ በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ትያትር እና ባህል አዳራሽ ተመረቀ፡፡ ስዩም ተፈራ ጽፎ ባዘጋጀው ቴአትር ላይ አበባው መላኩ፣ መስፍን አይፎክሩ፣ ማክዳ ኃይሌ፣ ሙሉነሽ ተሰማ፣ ፍፁም ተሾመ እና ግዛቸው መኩሪያ ይተውናሉ፡፡
አልመንሱር ፊልም ፕሮዳክሽን ከኢንስታሌሽን ፊልም ፕሮዳክሽን ጋር በመሆን ያቀረቡትና የደራሲና አዘጋጅ መቅደስ በቀለ (ማክዳ) “የሴቶች ጉዳይ” ፊልም ማክሰኞ ይመረቃል፡፡
የ105 ደቂቃ ርዝመት ባለው አስቂኝ የፍቅር ፊልሙ ላይ ሳምሶን ታደሰ (ቤቢ)፣ ህሊና ሲሳይ፣ ዮናስ አሰፋ፣ እስማኤል ኢብራሂም እና ሌሎችም ተውነዋል፡፡ የፊልሙ ዝግጅት ዘጠኝ ወራት ፈጅቷል፡፡