Monday, 05 March 2012 13:55

መሠረት ለፔንታ ወርቅ ተጠበቀች

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

በ14ኛው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ኢትዮጵያዊቷ መሰረተ ደፋር በ3ሺ ሜትር በመሳተፍ ለ5ኛ ተከታታይ ጊዜ የወርቅ ሜዳልያ እንደምትወስድ ተጠበቀ፡፡  አትሌት መሰረት ደፋር የምትሳተፍበት የዓለም የቤት ውስጥ የአትሌቲክስ ሻምፒዮና  ከ2 ሳምንት በኋላ በቱርኳ ከተማ ኢስታንቡል ሲካሄድ ከ178 አገራት የተውጣጡ 879 አትሌቶች ይሳተፉበታል፡፡ ከወር በፊት በቦስተን በተካሄደ የቤት ውስጥ የግራንድ ፕሪ አትሌቲክስ ውድድር በ3ሺ ሜትር የዓመቱን ምርጥ ሰዓት በ8 ደቂቃ ከ33.57 ሴኮንዶች በሆነ ጊዜ ያስመዘገበችው መሰረት ከዚህ ድሏ በኋላ በሰጠችው አስተያያት ፍላጎቷ በዓለም ሻምፒዮናው በርቀቱ 5ኛውን የወርቅ ሜዳልያ በመውሰድ የመጀመርያዋ ሴት አትሌት መባል መሆኑን ተናግራለች፡፡

በቤት ውስጥ የአትሌቲክስ ውድደሮች ውጤታማ በመሆን 10 ዓመታትን ያስቆጠረችው መሰረት ደፋር ከ2004 እኤ ጀምሮ በተሳተፈችባቸው የዓለም ሻምፒዮናዎች 4 የወርቅ ሜዳልያዎችን በመጎናፀፍ የከፍተኛ ውጤት ባለክብረወሰን ናት፡፡ አትሌት መሰረት ደፋር ከሁለት ዓመት በፊት በኬንያዋ አትሌት ሲልቪያ ኪቤት  በ8 ደቂቃ ከ41.24 ሰኮንዶች በሆነ ጊዜ የተመዘገበውን ሪኮርድ ልትሰብር እንደምትችል አንዳንድ መረጃዎች ገምተዋል፡፡ በ3ሺ ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር ከ8 ደቂቃ ከ30 ሴኮንድ በታች የመግባት ብቃት እንዳላትም አትሌቷ ትናገራለች፡፡

 

 

 

Read 3473 times Last modified on Monday, 05 March 2012 15:42