Sunday, 21 August 2016 00:00

የኡጋንዳ የፓርላማ አባላት የቅንጦት መኪና ግዢ ተቃውሞ ገጥሞታል

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(2 votes)

መንግስት መኪኖቹን ለመግዛት ከ190 ሚ. ዶላር በላይ መድቧል

    የኡጋንዳ መንግስት ለሁሉም የአገሪቱ የፓርላማ አባላት እጅግ ውድ ዋጋ የሚያወጡ የቅንጦት መኪኖች ለመግዛት ማቀዱ፣በአገሪቱ ዜጎችና በተቃዋሚ ፖለቲከኞች ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ መቀስቀሱን ኒው ቪዥን ድረገጽ አስነብቧል፡፡
በአገሪቱ ለሚገኙ 427 የፓርላማ አባላት የቅንጦት መኪናዎችን ለመግዛት  መንግስት በድምሩ ከ190 ሚሊዮን ዶላር በላይ መመደቡን የፓርላማው አፈ ጉባኤ ባለፈው ማክሰኞ ማስታወቃቸውን ተከትሎ፣ በርካታ ኡጋንዳውያን ተቃውሟቸውን ማሰማታቸውን ዘገባው ጠቁሟል፡፡ አፈ ጉባኤው ሬቢካ ካዳጋ፤ለፓርላማ አባላቱ መኪኖቹ መገዛታቸው ሃላፊነታቸውን በብቃት እንዲወጡ ያግዛቸዋል ቢሉም፣ የአገሪቱ ተቃዋሚዎችና አክቲቪስቶች ግን መንግስት አገሪቱ በኢኮኖሚ ችግር ውስጥ ተዘፍቃ ባለችበት ሁኔታ ይሄን ያህል ገንዘብ አውጥቶ የቅንጦት መኪና መግዛት አግባብ አይደለም በሚል ተቃውሟቸውን በተለያዩ መንገዶች አሰምተዋል፡፡
የዓለም ባንክ ባለፈው ሰኔ ወር ላይ ባወጣው ሪፖርት፣ የአገሪቱ ኢኮኖሚ በተለያዩ ውስጣዊና ውጫዊ ምክንያቶች አሳሳቢ ችግር ውስጥ ተዘፍቋል ማለቱን ዘገባው አስታውሷል፡፡

Read 1133 times