Sunday, 21 August 2016 00:00

“ብርድን ማሞቅ” የግጥም መድበል ነገ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

የገጣሚ ደቅሲዎስ ፍቅረ የግጥም ስብስቦችን ያካተተው “ብርድን ማሞቅ” የተሰኘ የግጥም መድበል ነገ ከጠዋቱ 3፡30 ጀምሮ በሀገር ፍቅር ቴአትር አዳራሽ ይመረቃል፡፡ መድበሉ በማህበራዊ፣ በፍቅርና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩ ከ90 በላይ ግጥሞችን የያዘ ሲሆን በ95 ገጾች ተመጥኖ፣ በ45 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡ በምርቃት ስነ ሰርዓቱ ላይ ከመፅሀፉ የተመረጡ ግጥሞች የሚነበቡ ሲሆን ገጣሚያን ስራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡና የተለያዩ የመዝናኛ ፕሮግራሞች እንደተዘጋጁ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 1832 times