Monday, 29 August 2016 10:46

“በዘመን ጥላ ስር” የግጥም መድበል ሰኞ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 የገጣሚ ፍፁም አማረ “በዘመን ጥላ ስር” የተሰኘ የግጥም መድበል ከነገ ወዲያ ከቀኑ 11 ሰዓት ጀምሮ በብሄራዊ ቴአትር ይመረቃል፡፡ መጽሐፉ የተለያዩ ዘመናትን የሚዳስሱ ከ75 በላይ ግጥሞችን ያካተተ ነው ተብሏል፡፡ በምረቃ ሥነስርዓቱ ላይ ገጣሚ ምስራቅ ተረፈ፣ አበባው መላኩና ሌሎችም ግጥሞቻቸውን የሚያነቡ ሲሆን ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ወግ እንደሚያቀርብና ከመፅሀፉ የተመረጡ ግጥሞች በተለያዩ ገጣሚያን እንደሚቀርብ ታውቋል።  መሶብ የባህል ሙዚቃ ቡድንም ዝግጅቱን በሙዚቃ ያደምቀዋል ተብሏል፡፡ በ116 ገጾች  የተመጠነው የግጥም መፅሐፍ፤ለአገር ውስጥ በ45 ብር፣ለውጭ አገራት በ17 ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 852 times