Monday, 29 August 2016 10:49

“ስደተኛው አስኮብላይ” ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 በደራሲ ኃይለማሪም አብዲሳ የተፃፈውና በአንድ ግለሰብ እውነተኛ ታሪክ ላይ የሚያጠነጥነው “ስደተኛው አስኮብላይ” የተሰኘ መፅሀፍ ለንባብ በቃ። መፅሀፉ የግለሰብ ታሪክ ላይ ቢያተኩርም ስለስደት ጦስ፣ ስለማይገባ የፍቅር መስዋዕትነት፣ ከልክ ስላለፈ ራስ ወዳድነት፣ ስለበቀልና ስለወንጀል መንስኤዎች የሚያስቃኝ ሲሆን ተተኪው ትውልድ ከታሪኩ በመማር ራሱን ከአላስፈላጊ ነገሮች እንዲጠብቅ ለማስተማር ታስቦ መፃፉን ደራሲው ጠቁመዋል፡፡ በ10 ምዕራፎች ተከፋፍሎ በ195 ገጾች የተቀነበበው መፅሀፉ፤ በ62 ብር ከ80 ሳንቲም ለገበያ ቀርቧል። ደራሲው ከዚህ ቀደም “ምርጥ የፍቅርና የፍልስፍና አባባሎች”፣ “የደም ሰንሰለት”፣ “ቀልድና ቁምነገር” እና “የፍቅር ስርቅታ” የተሰኙ መፅሐፍትን ለንባብ ማብቃታቸው ይታወሳል፡፡

Read 1214 times