Sunday, 04 September 2016 00:00

13 ሚ.ብር የወጣበት ‹‹ሰሬንደር›› የምሽት ክለብ ተመርቆ ተከፈተ

Written by  መንግሥቱ አበበ
Rate this item
(1 Vote)

    አሜሪካ ላስቬጋስ ለረጅም ጊዜ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው ሲኢኦ (Ceo) ክለብ ሁለተኛውን ቅርንጫፍ በአዲስ አበባ ‹‹ሰሬንደር›› በሚል ስያሜ ከፍቶ አስመረቀ፡፡ ድርጅቱ ከአንድ ዓመት በፊት “ሲኢኦ” ክለብ ቁጥር ሁለትን አዲስ አበባ ውስጥ ከፍቶ ውጤታማ በመሆኑ “ሰሬንደር”ን በ13 ሚሊዮን ብር ወጪ አደራጅቶ ከትላንት በስቲያ ጀምሮ እስከ ዛሬ በቀይ ምንጣፍ ስነስርዓት እያስመረቀ ነው ተብሏል፡፡ ኤድናሞል ጎን የሚገኘው ሰሬንደር ክለብ የላውንጅና የባር አገልግሎትም የሚሰጥ ሲሆን 500 ሰዎችን በአንድ ጊዜ ያስተናግዳልም ተብሏል፡፡ ለ60 ወጣቶች የስራ እድል የፈጠረው ክለብ ሰሬንደር፤ ዘመኑ ያፈራቸው የድምፅና የብርሀን ሲስተም የተገጠመለት ሲሆን ከ250 በላይ ህብረ ቀለማትን የሚያመነጩ ኤልኢዲፓናል የተሰኘ መሳሪያም እንደተገጠመለት የክለቡ ባለቤቶች ገልፀዋል፡፡ በሴኩሪቲና በመኪና ማቆሚያ በኩል ምቹና አስተማማኝ እንደሆነና ለከተማችን ህዝብ አማራጭ የመዝናኛ ቦታ ሆኖ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡ ክለቡ አገሪቱ ውስጥ ባሉ ስመጥር ዲጂዎች ይመራልም ተብሏል፡፡ ክለቡ ዘወትር ከማክሰኞ እስከ ቅዳሜ ከምሽቱ 6፡00 ሰዓት ጀምሮ አገልግሎት እንደሚሰጥ ባለቤቶቹ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

Read 1584 times