Sunday, 04 September 2016 00:00

በ48 ሚ ብር የተገነባው ሆቴል ሰለስት ኢትዮጵያ ዛሬ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

   ቦሌ አፍሪካ ጎዳና ከሸዋ ሱፐር ማርኬት ጀርባ፣ ወሎ ሰፈር፣ ተገንብቶ የተጠናቀቀው ‹‹ሆቴል ሰለስት ኢትዮጵያ›› ዛሬ ረፋድ ላይ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሀላፊዎች፣ ታዋቂ ሰዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ይመረቃል፡፡ በ500 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈው ሆቴሉ፤ 48 ሚሊዮን ብር እንደወጣበት የተገለፀ ሲሆን ተገንብቶ ለመጠናቀቅ 3 ዓመት እንደፈጀ የሆቴሉ ስራ አስኪያጅ ኤደን ሙሉወርቅ ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡ ሆቴሉ 19 ምቹና ዘመናዊ የመኝታ ክፍሎች፣ ደረጃውን የጠበቀ ባርና ሬስቶራን፣ቴራስ ሬስቶራንት፣ 70 ሰዎች የሚያስተናግድ የስብሰባ አዳራሽ፣ ሰፋፊና ምቹ የመታጠቢያ ክፍሎችና ጃኩዚዎችን የያዘ ሲሆን ክፍሎቹ በሙሉ ድምፅ የማያስተላለፍ ‹‹ሶሊድ በሮች›› እንደተገጠሙላቸው ስራ አስኪያጇ ተናግረዋል፡፡
ሆቴሉ ለጊዜው ከ60 በላይ ለሆኑ ሰዎች የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን በሙሉ አቅሙ ስራ ሲጀምር የሰራተኞቹ ቁጥር እንደሚጨምርና፤ ባለ 4 ኮከብ ደረጃ ያገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ ስራ አስኪያጇ ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡

Read 1621 times