እናት የማስታወቂያ ድርጅት ከጎተ የባህል ማዕከልና ከብሄራዊ ቤተ- መፃህፍትና ቤተ-መዛግብት ኤጀንሲ ጋር በመተባበር በበእውቀቱ ስዩም ‹‹ከአሜን ባሻገር›› የተሰኘ ታሪክ ቀመስ መፅሀፍ ላይ ነገ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በወመዘክር ውይይት ያካሂዳል፡፡ ለውይይቱ የመነሻ ሀሳብ የሚያቀርቡት በአ.አ.ዩ በፎክሎር የትምህርት ዘርፍ እጩ የዶክትሬት (PhD) ተመራቂ የሆኑት አቶ ገዛኸኝ ፀጋው ሲሆኑ ፍላጎት ያለው በውይይቱ ላይ እንዲሳተፍ እናት የማስታወቂያ ድርጅት ጋብዟል፡፡