Saturday, 03 September 2016 12:07

“የአመቱ የበጎ ሰው ሽልማት” አሸናፊዎች ዛሬ ይሸለማሉ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

     ዘንድሮ ለአራተኛ ጊዜ የሚካሄደው “የበጎ ሰው ሽልማት” አሸናፊዎች ዛሬ ከቀኑ 7፡30 ጀምሮ 22 ማዞሪያ በሚገኘው አቤል ሲኒማ አዳራሽ በሚካሄድ ስነ-ስርዓት ይሸለማሉ፡፡ “የበጎ ሰው ሽልማት” ኮሚቴ ሰብሳቢ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፤ ሰኞ ከሰዓት በኋላ በአቤል ሲኒማ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ በ10 ዘርፎች ማለትም በመምህርነት፣ በንግድና ስራ ፈጠራ፣ በማህበራዊ ጥናት፣ በሳይንስ፣ በቅርስና ባህል፣ መንግስታዊ የስራ ሀላፊነት በብቃት በመወጣት፣ በስፖርት፣ በኪነ-ጥበብ ፣ በሚዲያና ጋዜጠኝነት እና በበጎ አድራጎት ዘርፎች እጩ ሆነው ከቀረቡ ሶስት ሶስት ሰዎች አሸናፊዎች ይሸለማሉ፡፡ በሽልማት ስነ-ስርዓቱ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ ምሁራን፣ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚታደሙ ተገልጾዋል፡፡

Read 2049 times