Saturday, 10 September 2016 14:11

“የጨረቃ ጥላ” ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በአስራት ከበደ የተፃፈውና በኢህአፓ ታሪክ ላይ የሚያጠነጥነው “የጨረቃ ጥላ” የተሰኘ  መፅሀፍ ሰሞኑን ገበያ ላይ ዋለ፡፡ መፅሀፉ ከሁለት 10 ዓመታት በፊት ‹‹ሥር የያዘው ስር›› በሚል ርዕስ ተፅፎ መቀመጡንና አሁን የህትመት ብርሀን ማግኘቱን ደራሲው ጠቁመዋል፡፡   
በኢህአፓ ጊዜ የተከፈለው የህይወትና የአዕምሮ መስዋዕትነት ያስከተለው ችግር በመጽሃፉ ተዳስሷል ተብሏል፡፡ በ398 ገጾች የተዘጋጀው ይሄው መፅሀፍ፤በ81 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡  ፀሀፊው ከዚህ ቀደም ‹‹የምሽት እንግዳ›› የተሰኘ ልብ ወለድ መፅሀፍ ለንባብ ማብቃታቸው ይታወሳል፡፡

Read 855 times