Saturday, 10 September 2016 14:19

‹‹ባለፈረሱ ልዑል›› የህፃናት ቴአትር ዛሬ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 በደራሲና ዳይሬክተር ደረጀ ፍቅሩ ተፅፎ የተዘጋጀው ‹‹ባለፈረሱ ልዑል›› ቴአትር ዛሬ ረፋድ ላይ በአዳማ አሊያድ ሲኒማ ይመረቃል፡፡ በክልል ከተማ የተሰራ የመጀመሪያው የህፃናት ቴአትር እንደሆነ የተነገረለት ቴአትሩ፤በልዑል ዓለማየሁ ቴዎድሮስ ታሪክ ላይ የሚያጠነጥን የሙሉ ሰዓት ቴአትር ነው ተብሏል፡፡ በመረዋ የቴአትርና ፊልም ፕሮዳክሽን በተሰራው ቴአትር ላይ ረዳት አዘጋጁ ሄኖክ ታምራትን ጨምሮ ይርገዱ ሀይሌ፣ ብርሀኑ ሙጩ፣ ፀጋው ሀይሉ፣ ዘካርያስ በጋሻውና ሌሎችም ተውነውበታል፡፡ የቴአትሩ ደራሲና ዳይሬክተር ደረጀ ፍቅሩ፤‹‹ስርዬት›› በተሰኘው ተወዳጅ ፊልሙ ይበልጥ ይታወቃል፡፡

Read 953 times