Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 10 March 2012 09:19

ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ በጠና ታመው ኮርያ ሆስፒታል ገቡ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ላለፉት 11 ዓመታት ኢትዮጵያን በፕሬዝዳንትነት የመሩት እና የሥራ ጊዜያቸውን አጠናቀው ከሥልጣን ለመውረድ  የስድስት ወራት ዕድሜ የቀራቸው ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ በጠና ታመው ኮሪያ ሆስፒታል መግባታቸውን ምንጮች ጠቆሙ፡፡ በኮርያ ሆስፒታል የሚገኙ ምንጮቻችን ለአዲስ አድማስ እንደጠቆሙት፤ ፕሬዚዳንቱ ከትናንት በስቲያ በጠና ታመው በኮርያ ሆስፒታል ለሕክምና መግባታቸውን መመልከታቸውንና እስከ ትናንት ማምሻው ድረስ ተኝተውበታል ተብሎ የሚጠበቀው ክፍል በፕሬዝዳንቱ ጠባቂዎች ጥብቅ ጥበቃ ሲደረግበት እንደነበር ገልፀውልናል፡፡

በቤተመንግስት የሚገኙ ምንጮቻችንን ስለሁኔታው ጠይቀን፤ ፕሬዝዳንቱ ስብሰባ ሲመሩ እንደነበር የከፋ ሕመም ሳይሆን “ጉንፋን ቢጤ” ታመው ታክመው እንደተመለሱ  ቢገልፁልንም፤ ማተሚያ ቤት እስከገባንበት ሰዓት ድረስ ፕሬዝዳንቱ በኮሪያ ሆስፒታል እንደሚገኙ ምንጮች አረጋግጠውልናል፡፡ ፕሬዝዳንት ግርማ በመጪው ዓመት መስከረም ወር የሥልጣን ጊዜያቸውን አጠናቀው ከሥልጣን ይወርዳሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

 

 

Read 15267 times Last modified on Saturday, 10 March 2012 13:07