Sunday, 25 September 2016 00:00

‹‹ኑርልኝ›› ፊልም ለእይታ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

     በደራሲና ዳይሬክተር ስንታየሁ አባይ የተሰራውና በአቢሲኒያ ፊልም ፕሮዳክሽን የቀረበው ‹‹ኑርልኝ›› ፊልም በሁሉም ሲኒማ ቤቶች ተመርቆ ለእይታ መብቃቱን አዘጋጆቹ ገለጹ፡፡ የቤተሰብ ድራማ ዘውግ ያለው ፊልሙ፤የወላጆች አለመስማማት የሚያመጣውን ጦስ፣ የቸልተኝነት ውጤትንና የአባትና ልጅን የጠለቀ ፍቅር ያስቃኛል ተብሏል፡፡ በፊልሙ ላይ ሰለሞን ሙሄ፣ ሄኖክ ወንድሙ፣ ራሄል ይልቃል፣ ኤፍሬም ታደሰ፣ ታዳጊ ናፍቆት ብርሀኑና ሌሎችም ተዋንያን ተሳትፈውበታል፡፡ በመቅደስ መንግስቴ ፕሮዲዩስ የተደረገው ፊልሙ፤ በአሁኑ ሰዓት በግልና በመንግስት ሲኒማ ቤቶች እየታየ እንዳለና በቅርቡ በልዩ ፕሮግራም በድምቀት እንደሚመረቅ የፊልሙ አዘጋጆች ጨምረው ገልፀዋል፡፡ ደራሲና ዳይሬክተሩ ስንታየሁ አባይ ከዚህ ቀደም ‹‹አሜን›› የተሰኘ ፊልም የደረሰ ሲሆን ‹‹የሞግዚቷ ልጆች›› ፊልምን ማዘጋጀቱ ይታወሳል፡፡

Read 1979 times