Monday, 03 October 2016 08:19

የቻይንኛ ቋንቋ መማሪያ መፅሐፍ ነገ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  በኤልያስ አበራ የተዘጋጀውና ‹‹ኤላይጃ›› የሚል መጠሪያ የተሰጠው መሰረታዊ የቻይንኛ ቋንቋ መማሪያ መፅሐፍ ነገ ከ3፡00 ሰዓት ጀምሮ በሀገር ፍቅር ቴአትር አዳራሽ ይመረቃል፡፡
መፅሀፉ በሶስት ቋንቋዎች ማለትም በቻይንኛ፣ በአማርኛና በእንግሊዝኛ የተዘጋጀ ሲሆን መሰረታዊ የቻይንኛ ቋንቋ መማሪያ ቃላትን፣ የመኪናና የማሽነሪ መለዋወጫ እቃ ስሞችን፣ የግንባታ እቃዎንና ሌሎች ስያሜዎችን እንዳካተተ የመፅሀፉ አዘጋጅ ኤልያስ አበራ አስረድቷል፡፡
መፅሀፉ ሌሎች ቻይንኛ እንዲለምዱ ከማገዙ በተጨማሪ ቻይናዊያን አማርኛ እንዲለምዱም ይረዳቸዋል ብሏል፡፡ 96 ገጾች ያለው የመማሪያ መጽሐፉ፤በ89 ብር ከ99 ሳንቲም ለገበያ እንደቀረበ ታውቋል፡፡ 

Read 894 times