Monday, 03 October 2016 08:20

‹‹የጥሞና በሮች›› የስዕል አውደ ርዕይ ረቡዕ ይከፈታል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

የወጣቱ ሰዓሊና መምህር ቃልኪዳን ሾቤ፣የስዕል ስራዎች ለእይታ የሚበቁበት ‹‹የጥሞና በሮች›› የስዕል አውደ ርዕይ የፊታችን ረቡዕ በአሊያንስ ኢትዮ-ፍራንሴዝ ከምሽቱ 12፡30  ይከፈታል፡፡ በአውደ ርዕዩ ላይ 26 ስዕሎች ለእይታ የሚቀርቡ ሲሆን ስዕሎቹ በዋናነት ጥሞናንና እርጋታን የሚያንጸባርቁ ናቸው ተብሏል፡፡፡ አውደ ርዕዩ ለቀጣዩ አንድ ወር ለተመልካች ክፍት ሆኖ እንደሚቆይም ታውቋል፡፡ ሰዓሊው ከዚህ ቀደም በግሉ፣በጋለሪያ ቶሞካና ሀዋሳ በሚገኘው ዶልቼ ቪታ ሬስቶራንት የስዕል ጋለሪ፣ ስራዎቹን ለእይታ ያበቃ ሲሆን የአሁኑ ብቻውን ሲያቀርብ ለሶስተኛ ጊዜ መሆኑ ነው፡፡ ከስምንት ጊዜ በላይም ስራዎቹን ከሌሎች ሰዓሊያን ጋር በጋራ  ለእይታ ማብቃቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 634 times