ሚዩዚክ ሜይዴይ ኢትዮጵያ፣ ከኢትዮጵስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር፣ በኮ/ል አልኸንድሮ ዴል ባዬ ተፅፎ፣ በዶ/ር ተስፋዬ መኮንን ባይለዬኝ “ቀይ አንበሳ” በሚል በተተረጎመው መፅሐፍ ላይ ነገ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በብሄራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መፅሐፍት ኤጀንሲ አዳራሽ ውይይት ይካሄዳል፡፡ ለውይይቱ የመነሻ ሀሳብ የሚያቀርቡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ መምህር አቶ ዮናስ አሽኔ ሲሆኑ ፍላጎት ያለው በውይይቱ ላይ እንዲሳተፍ ሚዩዚክ ሜይዴይ ጋብዟል፡፡