Monday, 03 October 2016 08:26

‹‹ታሪክን በቅኔ›› መፅሐፍ ዛሬ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

     በደራሲ በሁሉም አለበል የተፃፈውና በቀኝ አዝማች ምስጋናው አዱኛ የህይወት ታሪክ ላይ የሚያጠነጥነው ‹‹ታሪክን በቅኔ›› የተሰኘ መፅሐፍ ዛሬ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ አምስት ኪሎ በሚገኘው በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን አዳራሽ ይመረቃል፡፡ በምርቃቱ ላይ የተለያዩ ኪነ-ጥበባዊ ዝግጅቶችም እንደሚቀርቡ ታውቋል፡፡ መፅሐፉ በዋናነት ቀኛዝማች ምስጋናው አዱኛ ከ1883 እስከ 1946 ማለትም ከምኒልክ እስከ ኃይለስላሴ ዘመነ መንግስት በኖሩባቸው አመታት ስለገጠሟቸው ግጥሞች፣ ስለ ቅኔዎቻቸው፣ከራስ ጉግሳ ወሌ ጋር ስለነበራቸው ግንኙነት፣ ስለ ትውልድ ቀያቸውና አስተዳደጋቸው በዝርዝር ይዳስሳል ተብሏል፡፡ በ164 ገጾች የተቀነበበው መፅሀፉ፤ለአገር ውስጥ በ69 ብር ከ99 ሳንቲም፣ለውጭ አገራት በ20 ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡ ደራሲዋ ከዚህ ቀደም በጋራና በግል በርካታ መፅሐፍትን ለንባብ ያበቃች ሲሆን በግል ካሳተመቻቸው መካከል ‹‹የተዋጡ ድምፆች››፣ ውስብስብ ውሎዎች፣ ‹‹የሸምበቆ ባህር›› እና “ሳምራዊ” የተሰኙት ይገኙበታል፡፡

Read 1405 times