Sunday, 09 October 2016 00:00

“አብዮቱና ትዝታዬ” ነገ ውይይት ይካሄድበታል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 በደርግ ሥርዓት ከከፍተኛ የአገሪቱ መሪዎች አንዱ በነበሩት ምክትል ፕሬዚዳንት ኮ/ል ፍሰሀ ደስታ በተፃፈው “አብዮቱና ትዝታዬ” የተሰኘ መፅሐፍ ላይ ነገ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በወመዘክር አዳራሽ ውይይት እንደሚካሄድ አዘጋጁ እናት የማስታወቂያ ድርጅት ገለጸ፡፡ ለውይይቱ መነሻ ሀሳብ የሚያቀርቡት የታሪክ ተመራማሪው አቶ አበባው አያሌው ሲሆኑ ፍላጎት ያለው ሁሉ በውይይቱ ላይ እንዲሳተፍ አዘጋጁ ተጋብዟል፡፡

Read 698 times