Sunday, 09 October 2016 00:00

“የተሰረቀው ህልም” ሐሙስይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

በካፒቴይን አልአዛር አያሌው የተፃፈው “የተሰረቀው ህልም” የተሰኘ መፅሐፍ የፊታችን ሐሙስ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ጀምሮ በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን አዳራሽ ይመረቃል፡፡ መጽሐፉ በሶስት ስርዓት-መንግስተ ውስጥ የተከወነ፣ የአሁኑን ዘመን ከወዲያኛው ያስተሳሰረ፣ በግለሰቦች ህይወት በኩል ትልቅ አገራዊ ታሪክን አምቆና አጭቆ የያዘ እውነተኛ ታሪክ መሆኑን ደራሲው በመግቢያቸው አስፍረዋል፡፡
በ360 ገጾች የተመጠነው መፅሐፍ፤  በ120 ብር እየተሸጠ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም ደራሲው ‹‹የተሰረቀው ህልምቁ--2››፣ ‹‹ደመኞች››፣ ‹‹ከእሳቱ ረመጡ››፣ ‹‹ቅድስት ሀገር ወይስ… እና ሌሎችም” የተሰኙ መፅሐፎችን ለማሳተም በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

Read 2020 times