Sunday, 09 October 2016 00:00

‹‹የግዕዝ ጥናት›› ነገ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(4 votes)

   የሐዲሳት መፅሐፍት ትርጓሜ፣ መምህርና የሶስተኛ ዓመት ነገረ-መለኮት ተማሪ፣ መጋቤ ሀዲስ አማኑኤል መንግስተአብ፣ ያዘጋጁትና በግዕዝ ቋንቋና ፊደላት፣ በዕብራይስጥ፣ በዓረብ፣ ትግረ፣ ትግርኛ፣ አማርኛና እንግሊዝኛ ፊደላት ላይ ጥልቅ ጥናትና ትርጓሜን የያዘው ‹‹የግዕዝ ጥናት›› የተሰኘ መፅሐፍ፤ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ አምስት ኪሎ በሚገኘው በቅርስ ጥናት ጥበቃ ባለስልጣን አዳራሽ ደራሲያን፣ ገጣሚያንና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ይመረቃል፡፡
የመፅሀፉ አዘጋጅ በተለይ የግዕዝ ፊደላት ላይ ጥልቅ ትንታኔ የሰጡ ሲሆን የግዕዝ ፊደል የተፃፈው ፊደል ድምፅ ኖሮት የሚነበብ፣ ያልተፃፈ የማይነበብበት፣ ራሱን ችሎ የቆመ ቋንቋ መሆኑን ጠቁመው እንግሊዝኛ ያለ አናባቢ ራሳቸውን ችለው መቆም እንደማይችሉ፣ የተፃፈ የማይነበብበትና ያልተፃፈ የሚነበብበት ቋንቋ መሆኑን አብራርተውበታል፡፡ በ365 ገጾች የተቀነበበው መፅሀፉ፤ለአገር ውስጥ በ80፣በ20 ዶላር ከ18 ሳንቲምለውጭ አገራት ይሸጣል፡፡
ፀሀፊው ከዚህ ቀደም ‹‹እንዚራ ስብሀት››፣ የተሰኘ መፅሀፍ ለንባብ ያበቁ ሲሆን ‹‹የእንዚራ ስብሃት ትርጉም›› እና “ፊደልህን ዕውቀቅ” ‹‹የተሰኙ መፅሀፎችን ለማሳተም በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡

Read 2948 times