Monday, 10 October 2016 07:15

ESOG-ACOG የፕሮጀክት ስምምነት

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(1 Vote)

 በ2016/ዓ/ም እንዲሰሩ ከወጡት እቅዶች አንዱ ጥራቱን የጠበቀ የህክምና አገልግሎት መስጠትና የስልጠናውን ሁኔታ በተሻለ መንገድ ማደራጀት የሚለው ስለነበር ከዚሁ ስትራ ጂክ ዶክመንት በመነሳት የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበርመሑሀ ከአሜሪካ የጽንስና ማህጸን ኮሌጅሑሀ ጋር ፕሮጀክት ለመንደፍ ችሎአል። ኮሌጁ የሚሰጠው የሙያዊ ድጋፍ ሲሆን በገንዘብ የሚደግፈው ደግሞ ሚቺጋን ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚገኘው Center for international reproductive health training የሚባለው ድርጅት ነው። በዚህ ስምምነት መሰረት ስራውን ለመጀመር ከሚያስችሉ ሁነቶች መካከል በአዲስ አበባ የማህበሩ አዳራሽ ከአሜሪካን የመጡት ባለሙያዎችና የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሕክምና ባለሙያዎች መስከረም 17-18/2009 ዓ/ም ስብሰባ አድርገው ነበር። ስለፕሮጀክቱ አላማና አተገባበር ዶ/ር ደረጀ ንጉሴ የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ፕሬዝዳንት እና በጤና ጥበቃ ሚኒስር የሚኒስትሩ ጽ/ቤት የጤና አማካሪን እና ዶ/ር ብርሀኑ ታደሰ የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር አሜሪካ ከሚገኘው የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ጋር በጋራ ለጀመሩት ፕሮጀክት በአሜሪካ በኩል የሚመሩ ባለሙያን ለአምዱ ጋብዘናቸዋል።
ዶ/ር ደረጀ እንደገለጹት ፕሮጀክቱ ለአምስት አመት የሚተገበር ሲሆን ዋና ዋና አራት ክፍሎችም አሉት።
በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የማህጸንና ጽንስ ሕክምና ድህረ ምረቃ ስልጠና በተሸለ ደረጃ እንዲሰጥ ማድረግ ትምህርት ቤቶቹ ያላቸውን የማስተማሪያ ዘዴ በተመሳሳይ እንዲሆን ማድረግን ያካትታል። በጽንስና ማህጸን ሕክምና ላይ የሚሰጠውን ተከታታይ ስልጠና ደረጃውንና ጥራቱን ጠብቆ እንዲሰጥ ማድረግ ፣
የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር በአመት ሁለት ጊዜ ሚያወጣው Journal of reproductive health ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆንና በዌብሳይትም እንደልብ እንዲነበብ የማድረግ ስራዎች እንዲሰሩ እንዲሁም ሳይንሳዊ ጽሁፉን ለሚያዩ ባለሙያዎች ስልጠና ይሰጣል ፣
ሳይንሳዊ ጽሁፉን መጻፍ የሚችሉ የጽንስና ማህጸን ሕክምናን በልዩ ሙያነት ለሚማሩ እና በስራው ላይ ያሉ ሐኪሞችም ለመጻፍና ለመመራመር የሚኖራቸውን ክህሎት ለማሳደግ እና የተሻለ ስራ ለመስራት እንዲሁም በምስራቅ አፍሪካ ደረጃውን የጠበቀ የምርምር ጽሁፍ የማቅረቢያ መጽሔት ማድረግ፣
የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ትምህርት በየትኛውም የህክምና ዩኒቨርሲቲ ቢኖርም የህክምና ትምህርታቸውን ሲጨርሱ ግን በአገር አቀፍ በተመሳሳይ ፈተና ተመዝኖ እንዲወጡ ከማድረግና ወደፊት ደግሞ ከጤና ጥበቃና ከትምህርት ሚኒስነር ጋር በሚኖሩ ስምም ነቶች የፈተናውን ውጤት የመያዝ እና እውቅና የመስጠት የመሳሰሉትን ነገሮች ከመን ግስት ተቋማት ጋር ጎን ለጎን በመሆን እና ወደፊት ደግሞ በሙያ ማህበሩ የሚያዝበትን ሁኔታ ከማመቻቸት አኩዋያ የታሰቡ ናቸው።
በፕሮጀክቱ ከታቀዱት ከላይ ከተጠቀሱት አበይት ነጥቦች ሌሎችም ተጉዋዳኝ እቅዶች መኖራቸውን ዶ/ር ብርሀኑ ታደሰ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበርን የኢንፎርሜሽን ክኖሎጂ ኃይል ለማጎልበት በጽህፈት ቤት ደረጃም ለመማሪያ የሚያስፈልጉ ነገሮችን ለመገንባት የሚያስችል፣
ለሴቶች ሕክምናና ከማህጸን እና ከጽንስ ጋር በተገናኙ እንዲሁም በአጠቃላይ የሴቶችን ጤንነት በተመለከተ የሚሰጡ ትምህርቶችንና ሌሎችንም ድጋፎችን ለማድረግ የሚያስ ችል የህዝብ ግንኙነት እና የኮሚዩኒኬሽን እቅድ በማውጣት ያንን እቅድ መተግበር እና አተገባበሩንም መቆጣጠር የሚያካትት ግንኙነት በዚህ ፕሮጀክት ውስጥ አለ።
 በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በተለያየ ደረጃ ላይ የሚገኙ አዳዲስና ነባር ትምህርት ቤቶች የማህጸንና ጽንስ ሐኪሞችን በማሰልጠን ላይ ይገኛሉ። ነገር ግን እነዚህ የተለያዩ ተቋማት በተመሳሳይ ደረጃ ላይ አይገኙም ። በዚህም ምክንያት አገሪቱ የምታፈራቸው ባለሙያዎች የተለያየ ደረጃ እንዲኖራቸው ስለሚያደርግ ጥራት ያለው ሕክምና ከመስጠት አኩዋያ ክፍተት እንዲመጣ ያደርጋል። ስለዚህም ይህንን ክፍተት በዋነኛነት በተሻለ ደረጃ መሙላት አስፈላጊ ነው። ይህን የጥራት ሐሳብ የፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስር በአምስት አመቱ የጤናው እቅድ ውስጥ እንዲካተት አድርጎታል። ከዚህም በመነሳት የማህጸንና ጽንስ ሕክምና ተማሪዎች በተሻለ ዝግጅት ሰልጥነው እንዲወጡ ማድረግና ስራ ላይ ያሉ ደግሞ የተሻለ ተከታታይ ትምህርት እንዲያገኙና ከዚህ በሁዋላ በእነዚህ ዝግጅቶች አማካኝነት ለተገልጋዩ ሕዝብ ጥራቱን የጠበቀ ግልጋሎት መስጠት እንዲያስችላቸው ማድረግ አንዱ ግብ ነው እንደ ዶ/ር ደረጀ ገለጻ።
 ዶ/ር ብርሀኑ እንደሚመሰክሩት የአሜሪካ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር በአለም ላይ በሰሜን አሜሪካ፣ በካናዳ ሜክሲኮን ጨምሮ ከሌሎች የአለም ሀገራት ከ/57.000/ሀምሳ ሰባት ሺህ በላይ አባላት ያሉት ሲሆን ለትርፍ የማይንቀሳቀስ ማህበር ነው። በአሜሪካ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር መጽሔት በአለም ላይ ካሉ ሳይንሳዊ መጽሔቶች ተነባቢነትን ካተረፉት ለምርምር ከሚረዱት መጽሔቶች ውስጥ አንዱ ነው። ይህንን መጽሔትም የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር አባላት በሙሉ ካለምንም ክፍያ መጠቀም እንዲችሉ በዚህ ፕሮጀክት አማካኝነት ሁኔታዎች ተመቻችተ ዋል። ስለዚህ ማናቸውም ኢንተርኔትን የሚጠቀሙ አባላት በማንኛውም ጊዜ ያንን ሳይንሳዊ መጽሔት ማንበብ ይችላሉ። በዚህ ሂደትም የራሳቸውን ክህሎት ለማዳበር፣ በሚያስተምሩበትም ጊዜ ምን ያህል ሳይንሳዊ እንደሆኑ ለማመን፣ በሕክም ናው ዘርፍም የሚሰጡት አገልግሎትም ሳይንሳዊ መሆኑን ለማረጋገጥ ይችላሉ።ስራ ላይ ያሉ ሐኪሞችም ከአሜሪካው ጆርናል በተከታታይ ሳይንሳዊ የሆኑ አዳዲስ ግኝቶችን ማንበብ እና ለተማሪዎቻቸው ለማካፈል እንዲሁም በስራቸው ላይ ለመተርጎም እድሉን ያገኛሉ። በአጠቃ ላይም ለሴቶቹ የሚሰጠው ህክምና ሙያ አገልግሎት ወደ አለም አቀፍ ደረጃ ከፍ እንዲል ያግዛል።
 ዶ/ር ደረጀ ንጉሴ የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ፕሬዝዳንት እንደሚሉት በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ቁጥር እንደማህበር አባል /306/ ሶስት መቶ ስድስት ቋሚ አባላት አሉ። በእርግጥ በማህበር አባልነት ያልተመዘገቡ የተወሰኑ ሰዎች መኖራቸው ስለሚታወቅ በድምሩ ከ/325-330/ ከሶስት መቶ ሀያ አምስት እስከ ሶስት መቶ ሰላሳ የሚደርስ ሐኪም አለ። ከዚህ ቁጥር እስከ 65 ኀ የሚሆኑት ሐኪሞች የሚገኙት በአዲስ አበባ ውስጥ ሲሆን ከአዲስ አበባም በአብዛኛው በግል የህክምና ተቋማት የሚሰሩ ናቸው። ከአዲስ አበባ ውጪ ባሉ ቦታዎች ላይ በተለይም ከክልል ከተሞች በሚወጣበት ጊዜ በቂ የሆነ የጽንስና ማህጸን ሐኪም የለም ማለት ይቻላል። ይህን የባለሙያ እጥረት ለማሟላት አስፈላጊውን ድጋፍ መሟላት ተገቢ ይሆናል።
ዶ/ር ብርሀኑ በስተመጨረሻ እንደተናገሩት ይህንን የባለሙያዎች እጥረትና በጥራት ህብረተሰቡን የማገልገል ክፍተት ለመዝጋት በኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበርም ሆነ በአሜሪካ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ወይንም ኮሌጅ በኩል ያሉ አመራሮች ፕሮጀክቱን ለመጀመር የተፈራረሙት ሰነድ በጊዜ የተገደበ ነው። ፕሮጀክቱን የሚደግፈው Center for international reproductive health training ደግሞ በየጊዜው የፕሮጀክቱን ተሳታፊዎች በተቀመጠላቸው መስፈርት መሰረት ሊያመጡ የሚገባቸውን ውጤት እንዲያሟሉ ጥረት ያደርጋል። ዋናው የፕሮጀክቱ ባለቤት የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ነው። የአሜሪካው የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ለኢትዮጵያው ማህበር አማካሪ ነው። ስለዚህም ዋናውን ፍላጎት የመግለጽ፣ ጥያቄ የማቅረብ ድርሻ የኢትዮጵያው ማህበር መሑሀ ነው። ከአሜሪካው የጽንስና ማህጸን ማህበር እንዲሁም ኮሌጅ እና ድጋፍ ሰጪው አካል በገንዘብ፣ በሰው ኃይልና በእውቀት የተደራጀ ኃይል በኢትዮጵያ በኩል የታቀደው ፕሮጀክት እውን እንዲሆን ጥረት ለማድረግ የተዘጋጀ ሲሆን ይህንን በተሟላ መልኩ የመጠቀም ኃላፊነት ደግሞ የኢትዮጵ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ነው።
ዶ/ር ደረጀ ንጉሴ በማጠቃለያቸው እንደገለጹት የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ከአሁን ቀደምም ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር የተለያዩ የስነተዋልዶ ጤና ግልጋሎቶችን እና የጨቅላ ሕጻናትን ደህንነት ለማስጠበቅ የሚረዱ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቶአል። ባለፈው ሀያ አምስት አመት ጊዜመሑሀ ከጤና ጥበቃ ሚኒስርና ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር የተለያዩ የስራ መመሪያዎችን በማውጣት ጥናታዊ ጽሁፎችን በማዘጋጀት ሙያዊ ድጋፍ በመስጠት ሲሰራ የቆየ ነው። አሁንም አዳዲስ ፕሮጀክቶችን በመንደፍ በመን ቀሳቀስ ላይ ሲሆን ከአሜሪካው የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ጋር ለመስራት ያቀደው እቅድ አንዱ ነው። የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር መጪው ዘመን ለህብረተ ሰቡ የተሸለ የስነተዋልዶ ጤና ግልጋሎት የሚሰጥበት እንዲሆን በፕሮጀክቱ የተነደፉትን ወደ ተግባር ለመቀየር የተሸለ ተግባር የሚያከናውንበት እንዲሆን የተጣለብንን ኃላፊነት እንደሚ ወጣ ተስፋ አለኝ ብለዋል።

Read 2273 times