Sunday, 16 October 2016 00:00

ኢትዮጵያ ትጠየቅ!

Written by  ዶ/ር ዘላለም እሸቴ
Rate this item
(2 votes)

ነገር ቢበዛ በአህያ አይጫንም። ስለዚህ ነገሬን አጠር
አድርጌ ላቅርብ። እነሆ!
የኢትዮጵያ ማንነት መገለጫው በዋነኛነት ምንድነው?
• ሕዝቡ ነው።
ታዲያ በሕዝቡ ስም (ኢትዮጵያ) ጥላ ስር መሪዎቻችን
ሁሉ የማይሰባሰቡት ለምንድነው?
• የታሪክ እስረኛ ሆነን በር በሌለው ጨለማ
እስር ቤት ውስጥ በመታለል ቁጭ ስላልን።
• ኢትዮጵያን መነሻ ሳናደርግ፣ ኢትዮጵያ
መድረሻ እንድትሆንልን ተመኝተን ጉም
ስንጨብጥ።
• ክልላችንን (አጥሩን) አፍርሰን፣ እንዳንያያዝ
አጥሩ ጎልያድ ሆኖብን ፍርሀት ስለሞላብን።
ሁሉም የሚስማማበት ጉዳይ ምንድነው?
• የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉም ብሔረሰብ
የጭቆና ሰለባ ሆኗል።
• የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉም ብሔረሰብ ደግና
ፈሪሃ እግዚአብሔር ያለው ነው።
• የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉም ብሔረሰብ
የተደባለቀና አብሮ ለዘመናት የኖረ ነው።
• የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉም ብሔረሰብ
ተባብሮ ታግሎ መንግስታትን ጥሏል።
• የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉም ብሔረሰብ
ተባብሮ ለጥቁር ሕዝብ ኩራት ሆኗል።
• የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉም ብሔረሰብ
አንድነታቸውን ዛሬም እያንፀባረቁ ነው።
• የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉም ብሔረሰብ
ሰብሳቢ ያጣ ቤተሰብ ሆኖ ተቸግሯል።
ሁሉም የሚገርመው የመሪዎች አባዜ ምንድነው?
• መንግስት ከፋፍሎ ይገዛል። ስልጣኑ
ጥሞታል።
• ተቃዋሚ ተከፋፍሎ ይታገላል። ለስልጣን
ቋምጧል።
የሚገርመው እውነታ ምንድነው?
• ፈጣሪ በተአምራቱ እስካሁን ብቻውን
አንድነቷን እየጠበቀ ነው።
• የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነቱን በራሱ
እያስተዳደረ ነው።
ፈጣሪ በቃችሁ ሲለን የሚሆነው ምንድነው?
• ልጆቿ አጥርን እያፈረሱ ይያያዛሉ።
• ምህረትና ፍትህ ይሳሳማሉ።
• ቁርሾ በፍቅር ይሟሟል።
• እውነት በእውን ይሰምራል።
• አሮጌውን ክፉ ታሪክ የሚያስረሳ አዲስ ታሪክ
ይሰራል።
• ልትሞት ነው የተባለችው ኢትዮጵያ
በትንሳኤ ትነሳለች።
• የኢትዮጵያ እናትነት እንደ ንጋት ጮራ ብርሃኗ
ይወጣል።
I am not Ethiopian first.
I am not Ethiopian second.
I am Ethiopian.
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!
(ኢሜል፦ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. )

Read 1438 times