Sunday, 23 October 2016 00:00

አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች የያዘ ዲኮደር

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  ዲኤስቲቪ በአይነቱ አዲስ የሆነና የዘመኑ ቴክኖሎጂ ያፈራውን ‹‹ኤክስፕሎራ›› የተሰኘ ዲኮደር ለገበያ አቀረበ። ዲኮደሩ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት ያሉት  ሲሆን አንድ ፕሮግራም እያሳየ ሌላ ፕሮግራም የመቅዳት፣ 10 ሰከንድ ወደ ኋላ መልሶ  የማሳየት፣ የስሎው ሞሽን እይታን ጨምሮ በርካታ አማራጮችን እንደያዘ የዲኤስቲቪ አፍሪካ ተወካዮች፣ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡
ከ220 ሰዓት በላይ የመቅዳት አቅም ያለው ዲኮደሩ፤ ያለማቋረጥ የዘጠኝ ቀናትን ፕሮግራሞች ቀርፆ የማስቀመጥ ብቃት እንዳለው ተገልጿል፡፡
ራሳችን ፈልገን ከምንቀዳው ውጭ፣ ራሱም ምርጥ ያላቸውን አንዳንድ ፕሮግራሞች ቀድቶ እንደሚያስቀምጥ የተነገረለት ዲኮደሩ፤ አንድ ሰው በጊዜ ማጣት ሊያልፉት የሚችሉ ፕሮግራሞች እንደ ማይኖሩ የዲኤስቲቪ ኢትዮጵያ ኃላፊዎች ተናግረዋል፡፡
ከኢንተርኔት ጋር የመቆራኘት ሀይል እንዳአለው የተገለፀ ሲሆን ኢንተርኔት ላይ ያሉ፤ ማናቸውም መረጃዎችን ወደ ዲኮደር ያመጣል ተብሏል፡፡
በቴሌቪዥን ኢንዱስትሪ ውስጥ ትልቅ አብዮት እንደፈጠረ የተነገረለት ዲኮደሩ፤ “The Best Innovative Technology›› የሚል ሽልማት ያገኘ ሲሆን እስከ ዛሬ በ10 ሺህ 943 ብር ለገበያ ይቀርብ እንደነበርና በአሁኑ ወቅት ተፈላጊነቱ በመጨመሩ ወደ 375 ብር ዝቅ ማለቱን ኃላፊዎቹ ተናግረዋል። “ደንበኞቻችን የአገልግሎት ተጠቃሚነታቸውን አያቋርጡም” ያሉት የዲኤስ ቲቪ ኃላፊዎች፤ ቅናሹ ለሶስት ወር ብቻ እንደሚቆይና ይህን ዲኮደር ለሚገዙ የአንድ ወር ነፃ አገልግሎት እንደሚሰጣቸው ገልፀዋል፡፡
ዲኮደሩ በአሜሪካ አገር በሲኒማ ቤት ሲታዩ የቆዩ ፊልሞችን ገና ወደ ዲቪዲ ሳይወርዱ ለማየት የሚያስችል አቅም እንዳለው የተገለፀ ሲሆን ዲኮደሩ ላይ ያለውን “ቦክስ ኦፊስ” የሚል ቁልፍ በመጫን ፊልሙን ማዘዝና አንድ ፊልም 59 ብር በመክፈል መመልከት ይቻላል ተብሏል፡፡ ዲኮደሩን በሸዋ ሱፐር ማርኬትና በዲኤስ ቲቪ ቅርንጫፍ ቢሮዎች መግዛት እንደሚቻልም ታውቋል፡፡

Read 2601 times