Sunday, 23 October 2016 00:00

በ‹‹አብዮቱና ትዝታዬ›› ላይ ሁለተኛው ክፍል ውይይት ነገ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

የቀድሞው መንግስት ም/ፕሬዚዳንት በነበሩት ኮ/ል ፍስሀ ደስታ በተፃፈው ‹‹አብዮቱና ትዝታዬ›› መፅሐፍ ላይ ከሁለት ሳምንት በፊት የመጀመሪያው ክፍል ውይይት የተደረገ ሲሆን ሁለተኛው ክፍል  ነገ በወመዘክር አዳራሽ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ እንደሚካሄድ እናት የማስታወቂያ ድርጅት ገለፀ፡፡
ለውይይቱ የመነሻ ሀሳብ የሚያቀርቡት የታሪክ ተመራማሪው አቶ አበባው አያሌው ሲሆኑ ፍላጎት ያለው ሁሉ በውይይቱ ላይ እንዲሳተፍ አዘጋጁ ጋብዟል፡፡

Read 1087 times