Sunday, 30 October 2016 00:00

“መድረክ” በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ የኮማንድ ፖስቱን ማብራሪያ ጠየቀ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(11 votes)

   የኢትዮጵያ ፌደራላዊ አንድነት መድረክ፤ ሀገሪቱን ያረጋጋል ተብሎ የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በተመለከተ ኮማንድ ፖስቱን ማብራሪያ እንደጠየቀ የፓርቲው ሊቀመንበር ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ ገለፁ፡፡
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በተመለከተ፤ “ማንኛውም ተቃዋሚ ፓርቲ የሀገርን ደህንነትን አደጋ ላይ የሚጥል መግለጫ መስጠት የለበትም” እንደሚል የጠቀሱት ፕ/ር በየነ፤ ኮማንድ ፖስቱ ዝርዝር ማብራሪያ እንዲሰጣቸው በደብዳቤ መጠየቃቸውን አስታውቀዋል፡፡
አዋጁ በተለይ በመሰረታዊ የፓርቲው ስራ ላይ ስለሚኖረው ተፅዕኖ፣ ለመገናኛ ብዙኃን ቃለ ምልልስና የአቋም መግለጫ ስለሚሰጥበት አግባብ እንዲሁም የፓርቲ ስብሰባዎች፡-  ማካሄድ በተመለከተ ግልፅ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጥያቄ ማቅረባቸውን ፕ/ር በየነ ገልፀዋል፡፡
“ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ፣ የአዳራሽ ስብሰባ፣ በየክልሉ አዳዲስ ፅ/ቤቶች መክፈት እንዲሁም ተቃዋሚዎች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በምን አግባብ መንቀሳቀስ እንደሚችሉ ማብራሪያ ጠይቀናል›› ብለዋል፡፡
ዝርዝር ጉዳዮችን በግልፅ እስከምንረዳ ድረስ የአቋም መግለጫዎችን ከማውጣት ተቆጥበን ቆይተናል ያሉት ሊ/መንበሩ፤ አዋጁን መተርጎም የሚችለው ኮማንድ ፖስቱ ብቻ መሆኑን ገልፀዋል፡፡




===========

Read 4946 times