Sunday, 30 October 2016 00:00

“ነገረ ፍቅር” መፅሐፍ ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  በወጣት ዳንኤል ዓለሙ የተዘጋጀውና በፍቅርና በሥነ ልቦና ጉዳዮች ላይ ያነጣጠረው “ነገረ ፍቅር” የተሰኘ መፅሐፍ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ገበያ ላይ ዋለ፡፡ መፅሐፉ ስለ ማፍቀር ሀይል፣ ስለ ፍቅርና ገንዘብ፣ ከሰዎች ጋር በፍቅር ስለሚኖርበት መንገድ፣ ይቅርታ ለፍቅር ስላለው ፋይዳና ሌሎች ተያያዥ ርዕሰ ጉዳዮች በስፋት ይዳስሳል ተብሏል፡፡
በሰባት ምዕራፎች ተከፋፍሎ በ178 ገጾች የተሰናዳው መፅሐፉ፤በ49 ብር ከ60 ሳንቲም ለገበያ ቀርቧል፡፡ ደራሲው  ከዚህ ቀደም “ፈተናን የማሸነፍ ጥበብ”፣ “ስኬታማ የፍቅር ህይወት”፣ “ገንዘብና ጭንቀት”፣ “ራስን የመለወጥ ምስጢር”፣ እና “ይህን ያውቁ ኖሯል ቁጥር 1”፣ የተሰኙ መፅሐፍትን ለንባብ አብቅቷል፡፡

Read 2213 times