Sunday, 30 October 2016 00:00

“የዘመን አሻራ” ዛሬ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

   በደራሲ ፋንታዬ እሸቱ የተጻፈው “የዘመን አሻራ” የተሰኘ ልቦለድ መፅሐፍ ዛሬ ጠዋት ከ3፡30 ጀምሮ በወመዘክር አዳራሽ ይመረቃል፡፡ የመፅሀፉ ታሪክ የፍቅር፣ የተንኮል፣ የታማኝነት፣ የክህደት፣ የፖለቲካ፣ የበቀልና የስለላ ሴራዎችን እያሰናሰለ ባልተጠበቀ መንገድ እንደሚቋጭ በጀርባ ማስታወሻው ላይ ሰፍሯል፡፡ በመፅሀፉ ምረቃ ላይ የተለያዩ ኪነ-ጥበባዊ ዝግጅቶች እንደሚቀርቡ የምረቃ ስነ-ስርዓት አስተባባሪዎች ጋዜጠኛ ጌጡ ታደሰና ጌታቸው አለሙ ገልፀዋል፡፡ “የዘመን አሻራ” በ2008 ዓ.ም መጨረሻ ላይ ለንባብ የበቃ ሲሆን በ333 ገጾች ተቀንብቦ፣በ90 ብር ከ95 ሳንቲም እየተሸጠ ይገኛል፡፡ ደራሲ ፋንታዬ እሸቱ ከዚህ ቀደም “ማን ይንገራት” የተሰኘ ቴአትር ደርሶ በማዘጋጀት በራስ ቴአትር ለእይታ ያበቃ ሲሆን  አጫጭር የቴሌቪዥን ድራማዎችን በመፃፍም ይታወቃል፡፡ 

Read 1913 times