Saturday, 05 November 2016 00:00

“ጥሞና” የመፅሀፍ አውደ ርዕይ ባዛር ሰኞ ይከፈታል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

   በብሄራዊ ቴአትር አርት ጋለሪ ከአንድ ዓመት በፊት የተጀመረውና “መፅሀፍ የህሊና የሰላም መንገድ” በሚል መሪ ቃል ይካሄድ የነበረው የመፅሀፍ አውደ ርዕይና ባዛር ሰኞ “ጥሞና” በሚል ርዕስ ለአራተኛ ጊዜ ይካሄዳል፡፡ ለሰባት ቀናት በሚቆየው በዚህ አውደ ርዕይ ላይ በርካታ የመሃፉ ነጋዴዎች አዳዲስና ያገለገሉ መፅሀፍትን ለአንባቢ ያቀርባሉ የተባለ ሲሆን ከ15 እስከ 50 በመቶ ቅናሽ ያደርጋሉ ተብሏል፡፡ በአውደ ርዕዩም ላይ ወጣት ገጣሚያን ስራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡ የአውደርዕዩ የአዘጋጅ “ሲልም የመፅሀፍት ንግድ ስራ አስኪያጅ አቶ ሰይፈዲን ሙሳ ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡

Read 740 times