Sunday, 06 November 2016 00:00

መቄዶንያ በSMS የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ሊጀምር ነው

Written by  መንግሥቱ አበበ
Rate this item
(1 Vote)

 • መኖሪያ ቤትና ሲኖ ትራክ፣ አይሱዙ፣ ሚኒባስና ሌሎች ሽልማቶች ----
                 • ገቢው ለ3ሺ አረጋውያን ማዕከል መገንበያ ይውላል ተብሏል
    መቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መረጃ ማዕከል፤ከኢትዮ ቴሌኮም በተሰጠው ፈቃድ መሰረት በቅርቡ በአጭር የጽሑፍ መልዕክት (SMS) የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም እንደሚጀምር አስታወቀ፡፡
ማዕከሉ ሲኤምሲ አካባቢ መንግሥት በነፃ በሰጠው 30ሺህ ካ.ሜ ቦታ ላይ የሚረዳቸውን አረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን ቁጥር 3ሺህ ለማድረስ የህንጻ ግንባታ መጀመሩን ጠቅሶ፣ ግንባታው በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ኢትዮ ቴሌኮም የሎተሪና የዕርዳታ ማሰባሰቢያ ሥራ በነፃ እንደፈቀደለት አስታውቋል፡፡  ኢትዮ ቴሌኮም ለ6 ወር የፈቀደለትን ነፃ የሎተሪና የዕርዳታ ማሰባሰብ ፕሮግራም በቅርቡ እንደሚጀምር ማዕከሉ ጠቅሶ፣ ኅብረተሰቡ፣ የዕርዳታ ማሰባሰብ ስራውን ለማገዝ በSMS መልዕክት ለሚልኩ የሞባይል ተጠቃሚዎች ሽልማት በመስጠት ወይም ሽልማት በመግዛት (ስፖንሰር ማድረግ) ይህን ታላቅ የዕርዳታ ማሰባሰቢያ ፕሮግም የተሳካ እንዲሆን የበኩላችሁን እገዛ እንድታደርጉ በትህትና እንጠይቃለን ሲል ተማፅኗል፡፡ ስፖንሰር የሚደረጉት ሽልማቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው ብሏል - መቄዶንያ፡፡
ዕለታዊ ሽልማት፡- አይፓድ፣ ሞባይል ስልኮች፣ ሳምንታዊ ሽልማቶች፡- ፍሪጅ፣ ቴሌቪዥን፣ ላፕቶፕ፣ ካሜራ፣ የሱፐር ማርኬት ኩፖኖች፣ የልብስ ካውያ፣ የጁስ መጭመቂያ ማሽን፣ ቢስክሌት፤ ወርሐዊ ሽልማቶች፡- ነፃ ኢንሹራንስ፣ ሶፋ፣ አረቢያን መጅልስ፣ ወንበርና ጠረጴዛ፣ ባጃጅ፣ ሞተር ቢስክሌት፣ የልብስ ማጠቢያ ማሽን፣ ነፃ የታሪካዊ ስፍራዎች ጉብኝት፣ ነፃ የሆቴል መዝናኛ ቆይታ፣ አይሱዙ፣ ሚኒባስ፣ የቤት አውቶሞቢሎች፣ የሦስት ወር ሽልማቶች፡- መኖሪያ ቤትና ሲኖ ትራክ፣ በበዓላት ወቅት ደግሞ፣ በሬ፣ በግ፣ ዶሮ፣ ወዘተ መሆናቸውን ጠቅሶ፣ ለርክክብ ስምምነት በ0920 28 92 73 ወይም 0949 49 49 49 በመደወል አስታውቁን ብሏል፡፡

Read 2277 times