አሌፍ መልቲ ሚዲያ ከሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ጋር በመተባበር፣ ‹‹ደጉ ሸገር›› የተሰኘ የመዝናኛና የመረጃ ፕሮግራም ማቅረብ ጀመረ፡፡ አዘጋጆች በሸገር ኤፍ ኤም ለረጅም አመታት አዝናኝና አስተማሪ ፕሮግራሞችን ሲያቀርቡ የነበሩት አንጋፋ ጋዜጠኞች ፋሲል ረዲና ተክለማሪያም ሀይሉ እንደሆኑ ታውቋል፡፡
አዲሱ የመዝናና ፕሮግራም የተለያዩ ዝግጅቶች የሚቀርቡበት ሲሆን ‹መነሀሪያ››፣ ‹‹የኛ ስጦታ››፣ ‹‹ኪስ››፣ ‹‹የኛ ጉዳይ››፣ ‹‹ወዶ ገብ››፣ ‹‹ጉሊት››፣ ‹‹መዚቃና ታሪክ›› የተሰኙ እንደሆኑ አዘጋጆቹ ለአዲስ አድማስ በላኩት መግለጫ አስታውቀዋል። ፕሮግራሙ በሸገር 102.1 ዘወትር አርብ ከምሽቱ 3፡30 እስከ 5፡00 እንደሚቀርብ ታውቋል፡፡