Sunday, 13 November 2016 00:00

የህይወት ተፈራ ‹‹Mine to Win›› ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

የቀድሞ የኢህአፓ ታጋይ በነበረችው ደራሲ ህይወት ተፈራ የተጻፈው ‹‹Mine to Win›› የተሰኘ ልብወለድ መጽሐፍ ትላንት ምሽት በዋቢሸበሌ ሆቴል ተመረቀ፡፡
የመፅሀፉ ታሪክ በባህላዊ ትውፊታችን በተለይም በቆሎ ተማሪ ህይወትና በት/ቤቱ ላይ የሚያጠነጥን ነው ተብሏል፡፡ 200 ገጾች ያሉት ‹‹Mine to Win›› መጽሐፍ፤ በ150 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡ መፅሐፉ ወደ አማርኛ ለመተርጎም በዝግጅት ላይ እንደሆነም ደራሲዋ ገልፃለች፡፡
ህይወት ከዚህ ቀደም በኢህአፓ የትግል ሂደትና በራሷ ተሞክሮ ላይ የሚያጠነጥን ‹‹Tower in The sky›› የተሰኘ መጽሐፍ ለአንባቢ ያደረሰች ሲሆን “ማማ በሰማይ” በሚል ወደ አማርኛ መተርጎሙ ይታወሳል፡፡

Read 3109 times