Sunday, 13 November 2016 00:00

የቆዳ ቦርሳ ፋሽን ሾው - በሸራተን ሆቴል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

ሸራተን ሆቴልና ካክተስ ኮሚዩኒኬሽን በመተባበር የሚያዘጋጁት የቆዳ ቦርሳዎች የፋሽን ትርኢት በመጪው አርብ ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በሸራተን አዲስ ይካሄዳል፡፡
በፋሽን ትርኢቱ ላይ 10 የቦርሳ ዲዛይኖች የሚቀርቡ ሲሆን ቦርሳዎቹ በፕሮፌሽናል ሞዴሎች ለእይታ ይቀርባሉ፡፡ በሌላው አለም የቦርሳ ትርኢት በየጊዜው ለእይታ የሚቀርብ ቢሆንም በአገራችን  የመጀመሪያው ትርኢት እንደሆነ የገለፀው ካክተስ ኮሚዩኒኬሽን፤ ትርኢቱ ቢለመድ ቦርሳዎቹ በአገራችን እንዲተዋወቁና የውጭ ገበያን እንዲስቡ ይረዳል ብሏል፡፡
የአሜሪካ ኤምባሲና ሄኒከን ቢራ ስፖንሰር ባደረጉት በዚህ ትርኢት ላይ፤ ሞዴሎች፣ በፋሽንና ዲዛይን ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶች፣ አርቲስቶችና ዲፕሎማቶች ይታደማሉ ተብሏል፡፡

Read 1448 times