Sunday, 13 November 2016 00:00

የአርቲስት ግሩም ኤርሚያስ ‹‹መሠረታዊ ትወና›› ተመረቀ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(3 votes)

አርቲስት ግሩም ኤርሚያስ ‹‹መሠረታዊ ትወና›› በሚል ርዕስ ያዘጋጀው ሙያዊ መፅሐፍ ባለፈው ሳምንት በካሌብ ሆቴል ተመረቀ።
መፅሀፉ ‹‹Basic Drama Project›› ከተሰኘ መፅሐፍ ላይ 12 የትወና መሰረታዊያንን መርጦ በመተርጎም የተሰናዳ እንደሆነ ታውቋል፡፡ ‹‹መሠረታዊ ትወና››፤ ከ9 ዓመት በፊት ለንባብ ቢበቃም፣ አዘጋጁ እንደገና የራሱን ተሞክሮ በመጨመርና በማሻሻል፣ እንደ አዲስ አሳትሞ አቅርቦታል፡፡ ተመስጦ፣ (Concentration)፣ ነገሮችን በምናብ መሳል (Imagination) እና ሌሎች መሰረታዊ የትወና ጥበቦችን የሚተነትነው መጽሐፍ፤ ለነባር ተዋንያን ራሳቸውን የሚያሻሽሉበት ሲሆን ለጀማሪዎች ደግሞ ወደ ዘርፉ መግቢያ ጥርጊያ መንገድ እንደሚሆናቸው ደራሲና ዳይሬክተር ፍፁም አስፋው በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ ተናግሯል።
በ104 ገጾች የተቀነበበው መፅሐፉ፤ በ40 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን ጃፋር መፅሐፍት መደብር እያከፋፈለው ይገኛል፡፡

Read 3320 times