Saturday, 19 November 2016 12:09

በጥር ለሚካሄደው የሥነ - ፅሁፍ ሽልማት፤ ዛሬ ምክክር ይደረጋል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

    ባህል፣ ኪነ ጥበብና ንባብን በማበረታታትና በማስተዋወቅ ስራ ላይ የተሰማራው ኢጋ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን፤ በመጪው ጥር ወር በሚያካሂደው የስነ ፅሁፍ ሽልማት ዙሪያ ዛሬ ረፋድ ላይ በጎተ ኢንስቲትዩት የምክክር ፕሮግራም ያካሂዳል፡፡ በምክክሩ ላይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን፣ የኢትዮጵያ ባህልና ቱሪዝም፣ የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም የሽልማት ውድድር ዳኞች፣ የሚዲያ ባለሙያዎች፣ በንባብ ላይ የሚሰሩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበርና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተው ሀሳብ ያዋጣሉ ተብሏል፡፡ የአዲ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቲያትር መምህር የሆኑት ፕ/ር አቦነህ አሻግሬ፣ በኢትዮጵያ የሽልማት ሂደቶች ላይ ያተኮረ ጥናት እንደሚያቀርቡ ታውቋል፡፡ በምክክር ፕሮግራሙ ላይ ድርጅቱ ሽልማቱን ለማዘጋጀት ያሰበበት አላማ፣ እስካሁን የሄደባቸው መንገዶች፣ የሽልማቶቹ ዘርፎችና ተወዳዳሪዎች የሚመረጡበት መስፈርት ይፋ ተደርገው፣ በታዳሚዎች የሚገመገሙ ሲሆን የማያስፈልጉት ይቀራሉ፤ የማሻሻያ ሀሳቦች ይጨመራሉ” ተብሏል፡፡  

Read 640 times