Sunday, 20 November 2016 00:00

የአማርኛ - እንግሊዝኛ “ዲክሺነሪ” ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(3 votes)

    በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ3ኛ ዓመት የህግ ተማሪ በሆነውና ማየት በተሳነው ሀብታሙ መለሰ የተዘጋጀው፤ “English - Amharic Dictionary of Subject Words” የተሰኘ መዝገበ ቃላት ገበያ ላይ ዋለ፡፡ መዝገበ ቃላቱ በተለይም ለ1ኛና ለ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች የሚያግዝ ሲሆን ከባዮሎጂ፣ ከፊዚክስ፣ ከሲቪክ፣ ከጂኦግራፊና ከታሪክ ዋና ዋና የሚባሉትን ቃላት መርጦ በመተርጎም ያዘጋጀው እንደሆነ ተገልጿል፡፡ 136 ገፆች ያሉት መዝገበ ቃላቱ፤ በ50 ብር እየተሸጠ ይገኛል፡፡ የመጽሐፉ አዘጋጅ ሀብታሙ መለሰ፣ እስከ ዘጠኝ ዓመቱ ማየት የሚችል የነበረና ከዚያ በኋላ ብርሃኑን ያጣ ቢሆንም በትምህርቱ፣ በማህበራዊ ኑሮውና በተለያዩ እንቅስቃሴዎች ንቁ ተሳታፊ ነው ተብሏል፡፡

Read 2215 times