Sunday, 20 November 2016 00:00

“የንፋስ ህልም” ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 ላለፉት በርካታ ዓመታት በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ የተለያዩ ወጎችና መጣጥፎችን በመፃፍ የሚታወቀው ደራሲ ሌሊሳ ግርማ፤ “የንፋስ ህልም” የተሰኘ የአጭር ልብ ወለዶች ስብስብ ሰሞኑን ለንባብ አብቅቷል፡፡ ለደራሲው የበኩር ሥራው የሆነው ይሄ መፅሃፍ፣በድጋሚ ታትሞ ገበያ ላይ ውሏል፡፡
መፅሐፉ፤ “የንፋስ ህልም እና ሌሎች የምናብ ታሪኮች” በሚል ርዕስ፣ 40 አጫጭር ልብ ወለዶችን ያካተተ ሲሆን በ192 ገፆች የተቀነበበ ነው፡፡ መፅሀፉ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአንባቢያን የደረሰው የዛሬ ሰባት ዓመት በ2002 ዓ.ም ሲሆን ለሁለተኛ ጊዜ የታተመውን መፅሀፍ ጃፋር መፅሀፍት መደብር ያከፋፍለዋል፡፡ ደራሲው ከዚህ ቀደም “አፍሮ ጋዳ”፣ “የሰከረ እውነት” እና ሌሎችም መፃህፍት ማሳተሙ ይታወሳል፡፡ 

Read 1662 times