Sunday, 27 November 2016 00:00

“አልሸሽም” መፅሀፍ ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

በጀርመናዊቷ ደራሲ ናስሪን ዚጋ የተፃፈውና በዩናስ ታረቀኝ “አልሸሽም” በሚል የተተረጎመው መፅሀፍ ሰሞኑን ገበያ ላይ ውሏል፡፡ በህፃናት ስደትና በመሰል ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥነው መፅሀፉ፤ የአንዲትን ህፃን ጉዳት መሰረት አድርጎ የመላውን የአፍሪካን ህፃናት ህይወት ይዳስሳል ተብሏል፡፡ ደራሲዋ ናስሪን ዚጋ የስነ - ልቦና ባለሙያ ስትሆን ቀደም ባሉት ጊዜያት በታንዛኒያ፣ ዛምቢያ፣ ማዳጋስካርና ሌሎች የአፍሪካ አገራት ከመኖሯም በላይ እ.ኤ.አ ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ ኢትዮጵያ ውስጥ መኖሯና “እርዳታ ለአፍሪካ” የተሰኘ ድርጅት አቋቁማ የተለያዩ ድርጅቶችን ስታግዝ እንደቆየች ተጠቁሟል፡፡ “አልሸሽም” በሚል የተተረጎመው መፅሀፍ በ183 ገፆች ተመጥኖ በ45 ብር እየተሸጠ ይገኛል፡፡

Read 1802 times