Sunday, 27 November 2016 00:00

“ቀጣይ የ4 ጡረተኞች ጭውውት” መፅሀፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

በኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ፕሮፌሰሩ ግርማ ሙልኢሳ የተፃፈው “ቀጣይ የ4 ጡረተኞች ጭውውት” የተሰኘ መፅሀፍ ሰሞኑን ለንባብ በቃ፡፡ መፅሀፉ በዋናነት ስለ ዓለማችን የፈላስፎች እይታ፣ የሂሳብና ሳይንስ ህብረት፣ ስለ አለማችን ያለፈው፣ የአሁኑና የወደፊቱ፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ መልካም ተፅዕኖ እና ዛሬና ነገ በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ የተሰናዳ መሆኑም
ታውቋል፡፡ በ156 ገፆች የተመጠነው መፅሀፉ፤ በ50 ብር እየተሸጠ ይገኛል፡፡

Read 2026 times