Saturday, 26 November 2016 13:21

“አባቶች እባካችሁ በሚስቶቻችሁ ይብቃ...”

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

“...ጊዜው ቀረብ ያለ ነው። አንድ ሴት ወደ ሆስፒታል ስትመጣ በምጥ ላይ ነበረች። ሴትየዋ በምን መንገድ የግብረስጋ ግንኙነት ታደርግ እንደነበር ሲታሰብ በጣም የሚደንቅ ነገር ነው። በብልትዋ ላይ በተሰራው መሰፋት የተነሳ የነበራት ቀዳዳ አንድ ጣት እንኩዋን አያሾልክም ነበር። ልጁ በምጥ በመገፋት የተነሳ ወርዶ ያንን የተጣበቀ ሰውነት ወጣጥሮ በዛች ቀዳዳ ጸጉሩ ይታያል። ሴትየዋ ምጥ ስለያዛት ኡኡ እያለች በስቃይ ልጁን ትገፋለች። ጠባሳው ከመቆየቱና ከመወፈሩ የተነሳ ተወጥሮ ያስፈራል። ስለዚህ ልጁም ታፍኖ እንዳይሞት ...ሴትየዋም ከስቃይ እንድትገላገል የተሰራው ቀላል ኦፕራሲዮን በጣም ከባድ ነበር። ሴትየዋ ስፌቱ ለምን ያህል ጊዜ እንደተሰራ እና መቼ እንደተሰራ ለመናገር ፈቃደኛ ባትሆንም ሰውነትዋ እንደሚያመላክተው በጣም በተደጋጋሚ መሰፋት እንደገጠማት ነው። እርግዝናው የመጀመሪያ በመሆኑ ያንን የተጋገረ ጠባሳ አስወግዶ ልጁን በሰላም ለማውጣት በየአቅጣጫው መከፈት ነበረባት። ያ ጠባሳ እጅግ የተጋነነና የተጋገረ ወፍራም ስለሆነ የማዋለድ ስራው እጅግ ፈታኝ ነበር። ባለሙያውም ላይ ሆነ ሴትየዋ ላይ የነበረው ጫና የሚረሳ አይደለም። ልጁን ለማውጣት የተሰራው ኦፕራሲዮን ሴትየዋ በጣም እንድትደማ ስላደረጋት ደም እንዲሰጣት እስከማስገደድ አድርሶ ነበር። ሰውነትዋን እንደነበር ለማስተካከል ከፍተኛ ጥረት ቢደረግም ጠባሳው እጅግ ወፍራም ስለነበር እንደተፈለገው መሆን አልቻለም። ሴትየዋን እንደገና ከዳነች በሁዋላም እንደተመለ ከትኩት ከሆነ በጥሩ ሁኔታ ወይንም ተፈጥሮአዊ መልኩን ለማስያዝ ስለአልተቻለ በጥሩ ሁኔታ አልዳነም። ”
 ትውስታ...ዶ/ር ማህሌት ይገረሙ
ከላይ ያነበባችሁት ዶ/ር ማህሌት ይገረሙ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የጽንስና ማህጸን ሐክምና እስፔሻሊስትና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሕክምና ትምህርት ቤት አስተማሪን የስራ ገጠመኝ ነበር። በሴት ልጆች ላይ የሚደርሰው ግርዛት የብልት ትልተላ እንደየአካባቢው የተለያየ ሲሆን ይህ አስከፊ የሆነውና በወሊድ ጊዜ ችግር የሚያስከትለው በተለይም በአፋር በሱማሌ እና ሌሎች ተመሳሳይ አካባቢዎች እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ።
ዶ/ር ፕሮፌሰር ሽፈራው ነጋሽ የጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔሻሊስት እና መምህር በበኩላቸው ሴት ልጆች ግርዛት ወይንም ትልተላ ከተፈጸመባቸው በሁዋላ በረጅም ጊዜ የሚፈጠርባቸው ችግር ምን እንደሚመስል እንደሚከተለው አብራርተዋል።
“...የብልት ትልተላ የደረሰባቸው ሴቶች በወደፊት ሕይወታቸው ከሚገጥሙዋቸው ችግሮች መካከል ፡-
ተደጋጋሚ የሆነ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን አንዱ ነው። የሽንት ቧንቧ ፣የሽንት ፊኛ፣ ፊንጢጣ እና ማህጸን መገናኘት ወይንም ፊስቱላ ሊገጥማቸው ይችላል።
ሽንትን መሽናት አለመቻልና ከዚህም ጋር በተያያዘ ፊኛ አካባቢ ጠጠር ሊፈጠር ይችላል።
ተደጋጋሚ የሆነ የማህጸን ኢንፌክሽን ይገጥማቸዋል።
የግብረስጋ ግንኙነትን ሲያደርጉ እጅግ ስቃይ ስለሚሰማቸው በሰላም መፈጸም አይችሉም። የግብረስጋ ግንኙነት አለማድረግ ደግሞ ሊፈጥር የሚችለው የስነ አእምሮ ችግር ከፍ ያለ ስለሆነ ስሜታቸው ይጎዳል።
የእርግዝና አለመከሰት ሊኖር ይችላል።
በማህጸን አካባቢ ፈሳሽ በአግባቡ የሚወገድበት ሁኔታ ስለሌለ በመጠራቀም ድንጋይ የሚፈጠርበት አጋጣሚም ይኖራል።
የሴት ልጅ ብልት ትልተላ ከፍተኛ ጠባሳ ስለሚኖረው የብልትን አካላዊ ቅርጽ የማበላሸት ሁኔታ ይኖራል።
ስለዚህም ከላይ በተገለጹት እና ሌሎችም ተመሳሳይ ችግሮች በተለይም ከባልዋ ጋር በተገቢው መንገድ የግብረስጋ ግንኙነት ማድረግ አለመቻልዋ እና እርግዝናንም የሚያውክ ነገር ሲገጥማት ሴትዋ እራስዋን እንደተሙዋላ ሴትነት ስለማትቆጥረው ሁልጊዜ አንድ ከባድ ነገር እንደጎደላት በመቁጠር እኔ እንደማንኛዋም ሴት የተሙዋላሁ አይደለሁም በማለት በስነአእምሮዋ ላይ ጠባሳ ይደርስባታል። ስለዚህ የሴት ልጅ ብልት ትልተላ ሴትዋን በአካልዋም በስነአእምሮዋም ጭምር ትልቅ ጉዳት የሚያደርስባት አስከፊ ድርጊት ነው።
ዶ/ር ማህሌት ይገረሙ እንደሚሉትም”...ልጅ የሚወጣበት የማህጸን ክፍል በጣም ተለጣጭ የሆነ ተፈጥሮ ያመቻቸችው የሰውነት ክፍል ነው። ስለሆነም ያልተገረዙ ሴቶች ካለምንም ተጨማሪ የህክምና እርዳታ በሰላም ይገላገላሉ። በእርግጥ አንዳንድ ከአቅም በላይ የሆኑ ችግሮች ማለትም ልጁ ትልቅ ከሆነ ወይንም አቀማመጡ ትክክል ካልሆነ እና የመሳሰሉት ችግሮች ሲያጋጥሙ ካልሆነ በስተቀር በምጥ ካለምንም ችግር ይገላገላሉ። ትልተላው የደረሰባቸው ግን ያንን ተፈጥሮአዊ የሰውነት ባህርይ ስለሚለውጠው እና ከፍተኛ ጠባሳ ስላላቸው ሰውነታቸው እንደልብ የመለጠጥ እድል አይኖረውም ። ስለዚህም፡-
አካባቢው በጠባሳ የሚድን በመሆኑ አረገዙም አላረገዙ ወይንም ወለዱም አልወለዱ ብልታቸው ጠባሳ ሆኖ ነው የሚገኘው።
ጠባሳው ከመጥበቁ የተነሳ እና ጡንቻው ሁልጊዜ ስለሚቆጣ የስነአእምሮ ዝግጁነት ይጎድላቸዋል። ስለዚህም ግንኙነት ማድረግ የማይችሉ ስለሆነ በጉልበት ወደማድረግ ይኬዳል። በጉልበት በሚፈጸምበት ወቅት ወንዱ እራሱ ሰውነቱ ስለሚቆጣ እና ስለማይመቸው ማድረግ አይችልም ። ይህ እንግዲህ በትዳር ውስጥ የሚያመጣው ቀውስ በቀላሉ የሚታይ አይደለም። ቶቹ ብልታቸው ሲተለተል ስሜት ሰጪ የሆነችውን ቁሽቄቈሽቋ ስለሚያስወግዱባቸው ሴቶሰበ ስለወሲብ ግንኙነት ምንም የሚያውቁት ነገር የለም። ከማርገዝና ለመውለድ ከመሰቃየት ውጪ የወሲብ ፍላጎት አይኖራቸውም። ስለዚህም እርካታ የሚባል ነገር አያውቁም።
በየግንኙነቱ ወቅት ሰውነታቸው ስለሚቆጣ እና ስለሚያማቸው ድርጊቱን ወደ መጥላት ከመሄዳቸው በላይ አርግዘው በወለዱ ቁጥር የተሰፋው እየተከፈተ እና እንደገና ከወለዱ በሁዋላ ተመልሰው ስለሚሰፉ ሕይወታቸው ሁልጊዜ ስቃይ ላይ ይሆናል።
የምጥ መዘግየት ፣ልጅ ቆይቶ የመወለድ፣ በመሳሪያ የመወለድ አጋጣሚ ይኖራል።
ጠባሳው የመተርተር አደጋ ይገጥመዋል። ሲተረተርም ጠባሳው በአካባቢው ሌላ የሰውነት ክፍልን እስከማበላሸት ይደርሳል።
ከወሊድ በሁዋላ የሽንት መቆጣጠር ችግር...የማህጸን መላላት ችግር ያጋጥማቸዋል።
ስለዚህም ይህ ድርጊት የአንድን ሰው የመኖር መብት የሚጋፋ ነው። ሐኪሞች ለማዋለድ ሲሉ ብልታቸውን ቢከፍቱም ቀደም ሲል እነርሱ እንደሰፉት ሳይሆን የብልታቸውን ቅርጽ አስይዞ መልሶ የመግጠም ስራ ይሰራል። አንዳንዶች በተለይ ለማህጸን ፈሳሽ ብቻ በጣም ትንህ ቀዳዳ አስቀርተው የሚሰፉት ስለሆነ ልጅ ለመውለድ ፈጽሞ አያስችልም። በዚህም ምክንያት ሌላ ችግር ሳይኖራቸው ብዙዎች ለፌስቱላ ይጋለጣሉ ። ስለዚህ በጤና ማእከል ሲወልዱ ተመልሶ የሚሰፋው ተፈጥሮአዊ ቅርጹን ይዞ ስለሆነ ቀድሞ የነበረውን ጠባሳ ማስወገድ ባይቻልም እንኩዋን ለወደፊቱ ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲቀጥሉ ያስችላቸዋል።
ዶ/ር ሽፈራው እንደሚገልጹት “...የሴት ልጅ ግርዛት የሚለው ቃል ትክክለኛ አይደለም። ግርዛት የሚለው ቃል በሕክምናውም ቋንቋ በእንግሊዝኛው ሰሽቈሰበቂሰሽቋሽቄቃ ማለት የማይፈለግ ነገርን ለማስተ ካከል የሚሰራ ስራ መገለጫ ሲሆን ይህ በሴት ልጅ ላይ የሚደርሰው የብልት መተ ልተል ግን አስፈላጊ ነገርን ማስወገድ ወይንም መጉዳት ስለሆነ በዚህ ሊገለጽ አይገባውም። ሴቶቹ ተፈጥሮአዊ የሆነውን የወሲብ ፍላጎት ወይንም ስሜት እንዲያጡ ከማድረጉም ባሻገር በህመም የሚሰቃዩበት፣ አልፎ ተርፎም ሕይወታቸውን ሊያጡ እስኪችሉ የሚያደርስ ስለሆነ ግርዛት በሚለው ቃል ሊገለጽ አይገባውም። ይህ ድርጊት ሊወገድ የሚችለው መንስኤውን ፣ የተጀመ ረበትን መነሻ ከስር ከመሰረቱ አውቆ ድርጊቱን የሚፈጽሙት ሰዎች እስኪያምኑ ድረስ ተከታታይ እና ዘላቂ ስራ መስራት ከተቻለ ብቻ ነው። ”
ዶ/ር ማህሌት በማጠቃለያቸው “..ከዛሬ አስር ወይንም ሰባትና ስምንት አመት ወዲህ የብልት ትልተላው በሚፈጸምባቸው አካባቢዎች በተለይም በከተሞች አካባቢ ሴት ልጆች መገረዛቸው ቀንሶአል። ምናልባትም የህጸናትን ሞት በመቀነሱ ረገድ አስተዋጽኦ አድርጎአል የሚል እምነት አለኝ። ምክንያቱም በግርዛት ወቅት በተለያዩ ምክንያቶች ብዙ ሕጻናት ይሞቱ ስለነበር ነው። በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ለውጥ አለ። ይህንን እስከመጨረሻው ለማስወገድ ደግሞ በተለይም ድርጊቱ በሚፈጸምበት አካባቢ ያሉ አባቶች ከፍተኛ ሚና አላቸው። በዚህ አጋጣሚ የማስተላ ልፈው መልእክት አለኝ።
“አባቶች፣ እባካችሁ በሚስቶቻችሁ ይብቃ! የብልት ትልተላ ወደልጆቻችሁ አይለፍ!”

Read 4701 times