Monday, 12 December 2016 12:23

“የአፍሪካ ህብረት መስራች አባቶች” ኤግዚቢሽን ሰኞ ይከፈታል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በቀድሞው ፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ አስተባባሪነት እና በኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ድጋፍ የተዘጋጀው የክቡር ዶ/ር ለማ ጉያ “የአፍሪካ ህብረት መስራች አባቶች” የስዕል ኤግዚቢሽን ሰኞ ታህሣስ 3 ቀን 2009 ዓ.ም ከቀኑ በ 4፡00 በኦሮሞ ባህል ማዕከል ይከፈታል፡፡ ይህንኑ ኤግዚቢሽኑን የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንር ዶ/ር ዶላሚኒ ዙማ በክብር እንግድነት መርቀው እንደሚከፍቱትም ታውቋል፡፡
በአውደ ርዕዩ ላይ በክቡር ዶ/ር ለማ ጉያ የተሳሉ የቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ፣ የጋናው ክዋሜ ንክሩማህ፣ የታንዛኒያው ጁሊዬስ ነሬሬ፣ የኡጋንዳው ጠ/ሚኒስትር ሚልተን አቦቴ፣ የግብፁ ገማል አብዱልናስር፣ የጊኒው አህመድ ሴኩቱሬ፣ የናይጄሪያው አላጂ ስር አቡበከር ታፋዋ ቤሉዋ፣ የኬኒያው ጆሞ ኬኒያታና ሌሎችም የ32ቱ የአፍሪካ ህብረት መስራች መሪዎች ምስል (ፖርትሬት) ለእይታ ይቀርባል ተብሏል፡፡
ከመስራች መሪዎቹ ምስል በተጨማሪም የአገራችን አትሌቶች የንግስት ቪክቶሪያ ምስልና የሌሎችም ታዋቂ ሰዎች ፖርትሬት ለእይታ እንደሚቀርብ ታውቋል። ይኸው ለ15 ቀናት ለእይታ ክፍት ሆኖ የሚቆየው ስዕል ኤግዚቢሽን መክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ኃላፊዎች፣ የተለያዩ አገራት ዲፕሎማቶች፣ የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። የመስራቾቹን ጨምሮ ከ850 በላይ ስዕሎች እንደሚቀርቡም ታውቋል፡፡

Read 908 times