Monday, 12 December 2016 12:25

የአየር መንገድን ታሪክ የያዘ መፅሃፍ ታተመ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

“The legacy of Ethiopian Airlines: as good as any if nor better 1960-1975” በሚል ርዕስ በኢንጂነር ኃይሉ አለማየሁ የተዘጋጀ መፅሐፍ ገበያ ላይ ውሏል፡፡ የመፅሀፉ ደራሲ በሲቪል አቪዬሽን ውስጥ በከፍተኛ ስልጣን ላይ ለብዙ አመታት የሰራና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ሆኖ ያገለገለ ሰው ነው፡፡
መፅሐፉን ለማዘጋጀት መረጃ በመሰብሰብና ጥናት በማድረግ ብዙ ዓመት እንደለፋ በመፅሐፉ መግቢያ ላይ ከመጥቀሱም ባሻገር በተለይ በኢትዮጵያ አየር መንገድ መስሪያ ቤት ውስጥ ላለፉ ወይንም በመስራት ላይ ላሉት ጥሩ ዋቢና መረጃ የሚለግስ ሥራ መሆኑን ጨምሮ ይገልፃል፡፡ መፅሀፉ በ25 ምእራፎችና በአያሌ ንዑስ ምዕራፎች የተደራጀ ሲሆን በ286 ገፆች ተቀንብቧል፡፡  አንጋፋ የሆነውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ታሪክ ከተመሰረተበት 1960 እ.ኤ.አ ጀምሮ ለአስራ አምስት ዓመት የተካሄዱትን ሂደቶች በስፋት ተንትኖ የሚያስነብብ ነው-የኢንጂነር ኃይሉ አለማየሁ መፅሃፍ፡፡ ደራሲው መኖሪያው ቦትስዋና እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 640 times