Monday, 12 December 2016 12:27

‹‹ባርቾ›› መፅሐፍ ላይ ነገ ውይይት ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 ሚዩዚክ ሜይዴይ ኢትዮጵያ፣ ከኢትዮጲስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር በደራሲ ህይወት እምሻው ‹‹ባርቾ›› የተሰኘ የታሪኮች ስብስብ መፅሐፍ ላይ ነገ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በወመዘክር አዳራሽ ውይይት ያካሂዳል። ለውይይቱ የመነሻ ሃሳብ የሚያቀርቡት የሥነ-ፅሁፍ ባለሙያው አቶ ነፃነት ተስፋዬ ሲሆኑ ፍላጎቱ ያለው ሁሉ በውይይቱ ላይ እንዲሳተፍ አዘጋጁ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡ ደራሲዋ በፌስቡክ ገጽዋ ላይ ከምታቀርባቸው ማህበራዊና ፖለቲካዊ ሂሶች በተጨማሪ በማራኪ የፈጠራ ድርሰቶቿም ትታወቃለች። ‹‹ባርቾ››የሚለው መጽሃፏ፤በፌስ ቡክ ገጽዋ በየጊዜው ስታስነብባቸው ከቆዩ ጽሁፎቿ መካከል የተመረጡ ታሪኮችን አካትቶ የያዘ ነው ተብሏል፡፡    

Read 1646 times