Monday, 12 December 2016 12:44

“አይቴል” ሞባይል 10ኛ ዓመቱን እያከበረ ነው

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 የሽያጭ ብልጫ ያሳዩ ነጋዴዎች ተሸልመዋል
                                         
      ሆንግኮንግ የሚገኘው ትራንሽን የተሰኘው የቻይና ኩባንያ ከሚያመርታቸው ስልኮች አንዱ የሆነው Itel ሞባይል መመረት የጀመረበትን 10ኛ ዓመት እያከበረ ነው፡፡ ክብረ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ከፍተኛ የ Itel ሽያጭ ያስመዘገቡ ቸርቻሪ ነጋዴዎች መገናኛ መተባበር ህንፃ ስር በተካሄደው ስነ ስርዓት ሽልማታቸውን ተቀብለዋል፡፡
ውድድሩ ከጥቅምት 9 እስከ ህዳር 10 ቀን 2009 ዓ.ም እስከ ኖቬምበር 19 ለአንድ ወር የተካሄደ ሲሆን በአዲስ አበባ. በመቀሌና በባህር ዳር የሚገኙ የሞባይል ስልኩ ቸርቻሪ ነጋዴዎች ተሳትፈው ከአንድ እስከ ሶስተኛ የወጡት ሽልማቶቻቸውን ከድርጅቱ ብራንድ ማናጀር እጅ ተቀብለዋል፡፡
በውድድሩ 1ኛ የወጣችው የአዲስ አበባዋ የአይቴል ነጋዴ ሄለን በጋሻው፤ መገናኛ መተባበር ህንፃ ስር በሚገኘው ሱቋ፣ በአንድ ወር ውስጥ 320 የአይቴል ስማርት ስልኮችን በመሸጥ 205 ሊትር የሚይዝና ዋጋው 13 ሺህ ብር የሆነ LG ማ ቀዝቃዣ ተሸልማለች፡፡
200 አይቴል ስማርት ስልኮችንና ከዚያ በላይ በመሸጥ ሁለተኛ ለወጡ ሁለት ነጋዴዎች ለእያንዳንዳቸው 32 ኢንች የሆነና 9 ሺህ 900 ብር የሚያወጣ LG ቴሌቪዥን የተሸለሙ ሲሆን ሶስተኛ የወጡ 4 የስልክ ነጋዴዎች እያንዳንዳቸው 3ሺ ብር ዋጋ ያላቸው የውሃ ማጣሪያዎች ተሸልመዋል፡፡
እ.ኤ.አ በ2007 ዓ.ም የተቋቋመው ትራንሽን ኩባንያ ከአይቴል በተጨማሪ ቴክኖ እና ኢንፊኒክስ የተሰኙ ስልኮችን የሚያመርት ሲሆን በተለይ በደቡብ እሲያና በአፍሪካ ከፍተኛ ተቀባይነት ማግኘቱንና በአፍሪካ ፋብሪካ ያለው በኢትዮጵያ ብቻ እንደሆነም ታውቋል፡፡
ድርጅቱ በአመት ከ 30 ሚ በላይ የአይቴል ስማርት ስልኮችን የሚሸጥ ሲሆን በየአመቱ ከ10 ሚ. በላይ አዳዲስ የአይቴል ስማርት ስልክ ተጠቃሚዎችን እያፈራ ነው ተብሏል፡፡ ድርጅቱ በዓለም ላይ በአይቴል ሞባይል ላይ የሚሰሩ ከ2500 በላይ ሰራተኞች እንዳሉትም በሽልማት ስነ ስርዓቱ ላይ ተገልጿል፡፡

Read 2371 times