Sunday, 18 December 2016 00:00

ከ“ገነት በስተ ምስራቅ” በአሜሪካዊ ማዕከል እውቅና አገኘ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

በአሜሪካዋ ካሊፎርንያ  የሚገኘው ‹‹ናሽናል ስቴንቤክ ሴንተር›› ለአቶ ጌታቸው አሻግሬ የልቦለድ ትርጉም እውቅና ሊሰጥ ነው፡፡  በአሜሪካዊ ደራሲ ጆን ስቴንቤክ East of Eden በሚል የተፃፈው ረጅም  ልቦለድ  በአማርኛ ከ‹‹ገነት በስተምስራቅ›› በሚል ርዕስ  በጌታቸው አሻግሬ  ተተርጉሞ ለገበያ የቀረበው ዘንድሮ ነበር፡፡
በብስራት ኤፍ ኤም በየሳምንቱ እሁድ በሚቀርበው የጥበብ ሞገድ ዋና አዘጋጅ ግሩም ሰይፉ ዋቢ መፅሃፍት በሚለው ፕሮግራም ካነጋገረ በኋላ ከ‹‹ናሽናል ስቴንቤክ ሴንተር›› ግንኙነት ፈጥሯል፡፡
የ‹‹ናሽናል ስቴንቤክ ሴንተር›› ዲያሬክተር ዶክተር ሱዛን ሺሊንግሎው፤ ለአቶ ጌታቸው በፃፉት ደብዳቤ ለትርጉም ስራው ተገቢውን እውቅና እንደሚሰጡ ገልፀዋል፡፡ ዶክተር ሱዛን፣ በማእከሉ ኦፊሴላዊ ህትመት የትርጉም ስራውን የሚመለከት ዜና እንደሚሰራጭ፤ ስለመፅሃፉ አተረጓጎምና ስለ ኢትዮጵያ ገፅታ አቶ ጌታቸው ያዘጋጀው አጭር መጣጥፍ  ለህትመት ይበቃል ብለዋል፡፡
ስቴንቤክ በ27 ረጃጅምና አጫጭር ልብወለዶች ስራዎቹ በ1940 እኤአ የኖቤል ሽልማትን እንዲሁም በ1962 የፑልቲዘር ሽልማትን የተቀበለ ታዋቂ ደራሲ ነው፡፡ 

Read 1295 times