Saturday, 17 December 2016 12:33

‹‹ሜክሲኮ ቡናና ሻይ›› መፅሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በጋዜጠኛ ዳንኤል ቢሰጥ የተፃፈው ‹‹ሜክሲኮ ቡናና ሻይ›› የተሰኘ መፅሀፍ ሰሞኑን  ለንባብ በቃ፡፡ በተለያዩ ርዕስ ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥኑ ወጎችን የያዘው መፅሀፉ፣ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኝና ለአዲስ አበባ እንግዳ የሆነ ወጣት የሚገጥሙትን የማህበራዊና ስነ-ልቦናዊ ፈተናዎች በሰላቅ፣ በግነትና በሽሙጥ እያዋዛ የሚተርክ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ በ173 ገጾች የተቀነበበው መፅሀፉ፤ በ65 ብር እየተሸጠ ይገኛል፡፡
ጋዜጠኛ ዳንኤል ቢሰጥ ከዚህ ቀደም ‹‹አፈር ብላ›› የተሰኘ የግጥም ስብስብና ‹‹የታች ሰፈር ቀልዶች›› የተሰኘ የቀልዶች ስብስብ መፅሀፍት ለንባብ ማብቃቱ የሚታወስ ሲሆን በአዲስ አበባ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ስር ባለው ‹‹አዲስ ቴሌቪዥን›› እና በ96.3 ኤፍ ኤም ሬዲዮ ላይ ድንቃድንቅ ዘገባዎችን በማቅረብም ይታወቃል፡፡

Read 1183 times