በቅርቡ ታትሞ ለአንባቢያን የቀረበው “አዙሪት” የተሰኘው ረጅም ልቦለድ እየተነበበ ነው፡፡ የታሪኩን መቼት አዲስ አበባ፣ አሰላ፣ ሐረርና ጅግጅጋ ያደረገው ልቦለዱ፣ የደርግ መንግሥትን የመጨረሻ ወቅቶችና ኢህአዴግ ሀገሪቱን መምራት የጀመረባቸውን የመጀመሪያ ዓመታት የታሪኩ ጊዜ አድርጓል፡፡ ልቦለዱ እንደ ሀገር ለዘመናት የምንኳትንበትን መንገድና መስበር ያቃተንን አዙሪት፣ ጭብጡ በማድረግ በሰፊው ይሞግታል፡፡ በ430 ገጾች ተቀንብቦ የቀረበው መጽሐፉ፤ በ99 ብር እየተሸጠ ነው፡፡
Sunday, 18 December 2016 00:00
“አዙሪት” እየተነበበ ነው
Written by ናፍቆት ዮሴፍ
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና