Sunday, 18 December 2016 00:00

የሰዎችን ባህሪ የሚተነትን መፅሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(41 votes)

 ሰዎች የተወለዱበትን ቀን መነሻ በማድረግ፣ ስለ ባህሪያቸውና ማንነታቸው በአስትሮሎጂ ጥበብ የሚተነትን ‹‹ሊንዳ ጉድማን፡ የፀሀይ ምልክቶች›› የተሰኘ መፅሐፍ ሰሞኑን ለንባብ በቅቷል፡፡
የትዳር አጋርን፣ የሠራተኛን፣ የአሰሪን፣ የልጆችንና የራስን ባህሪ ለማወቅ ያስችላል የተባለው መፅሃፉ፤ በተርጓሚ አብርሃም ጎዝጉዜ ነው ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ የተመለሰው፡፡ የስነ-ባህሪ ትንተናው የአስትሮኖሚና አስትሮሎጂ ሳይንስን መነሻ በማድረግ የተዘጋጀ መሆኑን በመግቢያው ላይ ያሰፈሩት ተርጓሚው፤ ጉዳዩ ሳይንስ ነው እንጂ ሰዎች እንደሚሉት ጥንቆላ አይደለም ሲሉ አብራርተዋል፡፡  
ሳይንሱ ሰፊ ምርምርን  የሚጠይቅ መሆኑን የገለጹት አብርሃም ጎዝጉዜ፤ ”የሰዎችን ባህሪ በቀላሉ አውቆ መልካም ግንኙነት ለመፍጠር ያስችላል” ብለዋል፡፡ ‹‹ሊንዳ ጉድማን፡ የፀሀይ ምልክቶች›› በ119 ብር ከ99 ሳንቲም ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 6883 times