Sunday, 18 December 2016 00:00

ባለፉት 2 አመታት 50 ሺህ ያህል የአይሲስ ታጣቂዎች መገደላቸው ተነገረ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ባለፉት 2 አመታት በሶርያና በኢራቅ 50 ሺህ ያህል የአሸባሪው ቡድን አይሲስ ታጣቂዎች መገደላቸውን አንድ የአሜሪካ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣን ማስታወቃቸውን ሮይተርስ ዘገበ፡፡
ባለስልጣኑ የተገደሉትን የአይሲስ ታጣቂዎች በተመለከተ “የተገመተው ቁጥር ይህን ያህል መድረሱ አሜሪካና ጥምር ሃይሉ በአሸባሪው ቡድን ላይ የከፈቱት ዘመቻ ምን ያህል ስኬታማ እንደሆነ ያሳያል” ማለታቸውንም ዘገባው አክሎ ገልጧል፡፡
 ከሁለት አመታት በፊት በኢራቅና በሶርያ የሚገኙ የአይሲስ ታጣቂዎች ቁጥር ከ20 እስከ 30 ሺህ እንደሚገመት የአሜሪካ የመረጃ ተቋም መግለጹን ያስታወሰው ዘገባው፤ ወታደራዊ ሃላፊው ተገድለዋል ያሏቸው ታጣቂዎች ቁጥር ከዚህ የሚበልጥ መሆኑን አስረድቷል፡፡ በሌላ በኩል አንድ የኩርድ ከፍተኛ የጦር መሪ፣ የታጣቂዎቹ ቁጥር ወደ 200 ሺህ እንደሚጠጋ  መናገራቸውን ዘገባው አስታውቋል፡፡

Read 1242 times